1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ምሥራቅ አፍሪቃ፣ የአዉሮጳ ሕብረትና አወዛጋቢው የነፃ ገበያ ድርድር

ሰኞ፣ ሰኔ 1 2007

የነፃ ገበያን በተመለከተ አዉሮጳ ሕብረት እና የምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት ማለት « ኬንያ፤ ሩዋንዳ፤ ብሩንዲ፤ ታንዛንያ እና ዩጋንዳ» ከአስር ዓመት በላይ ድርድር አካሄደዋል። ነፃ ገበያ ጉዳይ አዋቂዎች ይህን ድርድር ጥቅምና ጉዳቱ ያልተጤነበት ሲሉ ትችት ያቀርባሉ።

https://p.dw.com/p/1FdV3
Legehennen
ምስል dapd

[No title]

ለዚህ ምክንያታቸዉ ደግሞ ሃገራቱ ሸቀጦቻቸዉን ወደ ንግድ አጋር ሃገራቱ ሲልኩ የሚከፍሉትን ቀረጥ በተመለከተ ነዉ። ኬንያ ኤኮኖሚዬ ይቃወሳል ብላ በመስጋት ስምምነቱን አልፈረመችም።

Käsefarm im Ost-Kongo
ምስል cc-by-sa/Wendkuni


የኤኮኖሚ አጋርነት « EAC » የተሰኘዉ በአዉሮጳ ሕብረትና በምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት ድርድር መሰረት የምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት ወደ አዉሮጳዉ ሕብረት የሚልኩትን የሸቀጥ ምርታቸዉን የሚያስገቡት ከቀረጥ ነጻ በሆነ መንገድ ነዉ። በአንፃሩ የአዉሮጳ ሕብረት ሃገራት ምርታቸዉን ወደ ምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት ሲልኩ ቀረጥ እንደሚከፍሉ ነዉ የተመለከተዉ። ይህንን ሁኔታ ብረስልስ የሚገኘዉ የአዉሮጳዉ ኮሚሽን መቀየር ይፈልጋል። ይኸዉም ወደ ምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት የሚላከዉን የአዉሮጳ የሸቀጥ ምርት እስከ 82 % ከቀረጥ በነጻ ለማድረግና ፤ ቀስ በቀስ ከአዉሮጳ ወደነዚህ ምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት የሚገባዉ የሸቀጥ ምርት ያለምንም ቀረጥ እንዲገባ ማድረግ ነዉ። ኬንያ ባለፈዉ የጎርጎረሳዉያኑ 2014 ዓ,ም ኤኮኖሚዬ ያቃዉሳል በሚል ይህን ድርድር በፊርማ አላፀደቀችም። የአዉሮጳዉ ሕብረት በበኩሉ ስምምነቱ በፊርማ ተግባራዊ እንዲደረግ ያስገድዳል።

በናይሮቢ አቅራብያ ነዋሪ የሆነዉ ኬንያዊ አርቢ ጎድፍሪ ንጋንጋ 1500 ዶሮዎችና የስድስት ላሞች ባለቤት ነዉ። ጎድፍሪ እንደ አብዛኞቹ የኬንያ ገበሪ ወይም ከብት አርቢዎች በአነስተኛ ምርት የሚተዳደር ነዉ። ጎድፍሪ ከአዉሮጳ የሚመጣዉ ሸቀጥ የኑሮ መሰረቱን እንዳያናጋ አስፈርቶታል።

« እነሱ የኛን ምርት መሸመት አለባቸዉ። እንቁላል፤ ወተትና ዶሮ። ነገር ግን እነሱ በቴክኖሎጂ እጅግ መጥቀዉ ስለተራመዱ ምርታቸዉን እጅግ በረከሰ ሁኔታ እኛዉጋ መሸጥ ይችላሉ»

በአዉሮጳ ሕብርት እና በምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት መካከል ባለፈዉ ዓመት የተደረሰዉ ስምምነት የሚያስገኘዉ ጥቅምን ብቻ እንደሆነ ነዉ የተነገረዉ። በጎርጎረሳዉያኑ 2013 ዓ,ም ከአዉሮጳ ሕብረት ለኬንያ የተሰጠዉ አንድ የማስታወቅያ ፊልም እንደያመለክተዉ ስምምነቱ የጥሩ ገበያ በር መክፈቻ ብቻ ሳይሆን፤ ከዝያም በላይ እንደሆነ ነዉ።

« ምስራቅ አፍሪቃን ከአዉሮጳ ሕብረት ጋር ትክክለኛ የሆነ የአጋርነት የሥራ ትብብር ቢኖራት፤ ለመዋዕለ ንዋይ ፍሰት ጥሩ ሁኔታን የሚያመቻችና መንገድን የሚከፍት ነዉ»
ከአዉሮጳ ሕብረት ጋር የሚደረግ የነፃ ገበያ ስምምነትን በተመለከተ ኬንያ ዉስጥ የሚናፈሰዉ መጥፎ ወሪ ብቻ ነዉ። የናይሮቢዉ መንግሥትም ስምምነቱን ተግባራዊ ማድረግን አይፈልግም። ምክንያቱ ደግሞ የሃገሪቱ ዋንኛ የገቢ ምንጭ የሆነዉ የግብርና ዉጤት ከአዉሮጳ በአነስተኛ ገንዘብ ከሚመጣዉ የፍራፍሪና የአታክልት ምርት ሸቀጥ መወዳደር አይችልም በሚል ፍርሃት ነዉ።
የኬንያ የሰብዓዊ ጉዳዮች ኮሚሽን ባልደረባ ፍሪድሪክ ንጂሁ እንደሚሉት የምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት በአዉሮጳዉ ሕብረት ምርታቸዉን ከቀረጥ ነጻ ማቅረብ ቢችሉም ድርድሩ እጅግ መጥፎ አይነት ነዉ።

« ይህ ድርድር እጅግ መጥፎ አይነት ነዉ። የአዉሮጳዉ ሕብረት የምስራቅ አፍሪቃዉያኑ ሃገራት እንዲያደርጉ የሚጠብቀዉን ነገር ማየቱ የሚቻልና የማይሆን ነገር ነዉ። በተለይ 82 % ሸቀጥ ያለቀረጥ እንዲገባ መፈለጉ ። ይህ ማለት በመጭዉ 15 ዓመት ዉስጥ ቀረጥ የሚለዉ ነገር ይነሳል ማለት ነዉ።
በኬንያ የሚገኝ አንድ የኤኮኖሚ ተቋም ባወጣዉ ጥናት መሰረት ኬንያ ለእድገትዋ ድጋፍ ሊሰጣት የሚችል በዓመት ከ 100 ሚሊዮን ይሮ በላይ ገንዘብን ታጣለች። ይህ የነፃ ገበያ ስምምነት ወደ አዉሮጳ ሕብረት በሚገቡት የሸቀጥ ምርት ላይ አዲስ የቀረጥ ክፍያን ይጠይቃል። በአንፃሩ የምስራቅ አፍሪቃዉያኑ ሃገራት ኤኮኖምያቸዉ እንዳይጎዳ ለመጀመርያዉ ጊዜ ይህን ማድረግን አይሹም። እንደ አዉሮጳ ሕብረት አመለካከት ደግሞ ይህ ሁሉ ፍራቻ መሰረተ ቢስ ነዉ።
የተመድ የኤኮኖሚ ጉዳይ ምሑራን በበኩላቸዉ ይህ ስምምነት ለአፍሪቃዉያኑ ሃገራት ምንም አይነት እድልን የማያስገኝ በአንጻሩ በአዉሮጳ ሕብረት ሃገራት ገበያ ሳብያ የሃገራቱ ኤኮኖሚ ስጋት ላይ ይንጠለጠላል ሲሉ ምልክታቸዉን ይገልፃሉ።

Airbus Logo
ምስል DW/J. Raupp
Mbororo Nomaden aus dem Wodaabe Stamm
ምስል Eric Cabanis/AFP/Getty Images


አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ