1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ማፊ ፣ ትርፌ እና እከ ( የቤቶች ድራማ ተዋንያን)

ዓርብ፣ ጥር 2 2006

ቤቶች የተሰኘው ድራማ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጪ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ዝናን አትርፏል። ምዕራፍ፣ ትርፌ እና እከ የዛሬው እንግዳዎቻችን ናቸው።

https://p.dw.com/p/1Aomc
Symbolbild Drama Theater Schauspielerei
ምስል Fotolia/A. Burmakin

ገሊላ ርዕሶም በቤቶች ድራማ ላይ የአቶ ዘሩ የመጀመሪያ ሴት ልጅ- ማፊን ሆና ትጫወታለች። ማፊ እና ገሊላን የሚያመሳስላቸው አንድ ነገር አለ ትላለች ገሊላ፤ ለፊልም ስራ ያላቸው ፍቅር። ገሊላ ተዋናይ እና ተማሪ ናት። ምንም እንኳን በትወናው ታዋቂነት ብታተርፍም፣ በመድሃኒት ቀማሚነት የጀመረችውን ትምህርቷን የማጠናቀቅ ዓላማ አላት። ዓላማ አላት። ከዚህም ባለፈ ወጣት ተዋንያኑ በድራማው ለሌሎች ወጣቶች ሊያስተላልፉት የሚፈልጉት እና የሚያክሉት ነገር አለ ትላለች።

ሌላው ተዋናይ፤ ንብረት ገላው ይባላል። ብዙዎች እከን ሆኖ ሲጫወት ያውቁታል። እሱ እንደሚለው ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ነው። የገጠር እና የክፍለ ሀገሩን ኑሮ ኬት አወቀው? አጫውቶናል።

ሌላዋ የምግብ ነገር ከተነሳ፤ ስሟ ሳይጠራ የማያልፈው ዘርፌ ናት። ተዋንያዋ ሰብለ ተፈራ « ስራ ስለሆነ ብቻ ነው እንጂ ሰብለ ለዳቦ ግድ የላትም» ትላለች። ከዚህስ ሌላ ሰብለ ማን ናት?

ልደት አበበ

አርያም ተክሌ