«ማፊ» ማህሌት አፈወርቅ19 መስከረም 2004ዓርብ፣ መስከረም 19 2004በርካታ ኢትዮጵያውያን «ማፊ» በሚለው መጠሪያዋ ያውቋታል ሙሉ ስሟ ማህሌት አፈወርቅ ነው። የልብስ ቅድ ባለሙያ፣ እንዲሁም የመድረክ ሰው ነች።https://p.dw.com/p/RoVBሙኒክ/ጀርመን የተዘጋጀው የፋሽን ትርኢትምስል Goethe-Institut/Bálint Meggyesiማስታወቂያማህሌት አፈወርቅ አዲስ አበባ ነው ተወልዳ ያደገችው። ወጣቷ ገና በልጅነቷ የልብስ ቅድ ዲዛይን ስራ አድናቂ ነበረች። ባለፈው ግንቦት ወር በሙኒክ/ጀርመን በተዘጋጀው የፋሽን ትርኢት ከአምስት ኢትዮጵያዊውያን የልብስ ቅድ ባለሙያዎች ወይም ዲዛይነርስ ጋር በመሆን ስራዎቿን አስተዋውቃለች። የወጣቶች መድረክ እንግዳ ነች። ዝግጅቱን ያድምጡ። ልደት አበበ ነጋሽ መሐመድ