ሚዲያ እና ዴሞክራሲ ላይ ያተኮረው ውይይት
ሰኞ፣ መጋቢት 2 2011የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅ ጃዋር መሐመድ፣ የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቭዥን ጋዜጠኛው ሲሳይ አጌና ጨምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት በመገናኛ ብዙኃን እና በዴሞክራሲ ላይ ያተኮረ ውይይት አዲስ አበባ ላይ ተካሒዷል።
በውይይቱ ጃዋር መሐመድ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን የከፋ አደጋ አለማድረሳቸውን ተናግሯል። ጃዋር "ምኅዳሩ ከልክ በላይ በሰፋበት፣ ይኸን ምኅዳር ግልፅ የሆነ ሕግጋት እና አሰራር በመንግሥትም ሆነ በሚዲያው ባልተቀመጠበት ሒደት ውስጥ እስካሁን እኔ የማያቸው አብዛኞቹ ሚዲያዎች የሕዝባዊ ግጭትን በመንግሥት እና በአገር ደሕንነት ላይ አደጋ የሚያደርስ አሰራር ውስጥ" አልገቡም ሲል ተናግሯል።
በመድረኩ ተሚሰራበት ተቋም ጋር በተያያዘ ተቃውሞ የገጠመው ጋዜጠኛ ሲሳይ አጌና "የመንግሥት ባለሥልጣናት አካባቢ መረጃ ለማግኘት የሚደረጉ ዝግ ኹኔታዎች አሉ። እነዚያ ኹኔታዎች የሚሻሻሉ ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ ታይቶም ተሰምቶም በማይታወቅ መልኩ ሐሳብን የመግለፅ ነፃነት በከፍተኛ ደረጃ ተከፍቷል። ይኸ ነፃነት ግን ወደ መጥፎ አቅጣጫ እየሔደ መሆኑ ማሳሰቡ ተገቢ ይመስለኛል" ብሏል።
በጠቅላይ ሚኒስቴር ፅህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በበኩላቸው "በጋዜጠኝነት እና በአራማጅነት መካከል ትክክለኛ መስመር እና ድንበር ወጥቶ የሚሔዱበት ኹኔታ በውስንነት የሚታይ ነው" ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።
ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር
ተስፋለም ወልደየስ
እሸቴ በቀለ