ሙስና በኢትዮጵያ
ዓርብ፣ ግንቦት 10 2010ማስታወቂያ
የሀገራትን የሙስና ደረጃ የሚያወጣው ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የተባለው ዓለም አቀፍ ድርጅት በጎርጎሮሳዊው 2017 ኢትዮጵያን በሙስና ከ180 ሀገራት፣117ተኛ ደረጃ ላይ አስቀምጧል። የኤኮኖሚ ባለሞያዎች እንደሚሉት ሙስና የሀገሪቱን እድገት ከሚያጓትቱት ችግሮች አንዱ እና ዋነኛው ነው። ዶቼቬለ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው ምሁራን በተለያዬ መንገድ የሚፈፀመው ሙስና በኢትዮጵያ ታሪክ ባልተለመደ ሁኔታ እያደገ ነው ሲሉ አስረድተዋል። በሀገሪቱ ሙስና የህዝባዊ አመጽ መንስኤ እንደነበረም የቅርብ ጊዜዎቹን ተቃውሞዎች ምሳሌ አድርገው ተናግረዋል። መክብብ ሸዋ ከዋሽንግተን ዲሲ ዝርዝሩን ልኮልናል።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ