ሙስና በቱርክ
ሐሙስ፣ ጥር 1 2006ማስታወቂያ
በቱርክ ሀገር በስልጣን በመባለግና በሙስና ተከሰው በርካታ ሰዎች ከስልጣናቸው ከተባረሩ ወዲህ በሀገሪቱ የኃይል አሰላለፍ ወዴት እንዳጋደለ መገመቱ አስቸጋሪ ሆኗል። የፖሊስ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖችና አዛዦችን እንዲሁም ሚንስትሮችን ጨምሮ ወደ 2 ሺህ የሚጠጉ ባለስልጣናት ቱርክ ውስጥ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ተደርጓል። በሙስና ጽዳት ዘመቻው ፊታውራሪ ሆነው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የሀገሪቱ አቃቤያነ ሕጎችና ዳኞችም ከስራቸው ተባረዋል። የበርልኒ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ከቱርክ ውጪ በብዙ መቶ ሺህ ቱርኮች በሚኖሩባት የበርሊንከተማ ተዘዋውሮ የቱርክ ተወላጆችን አነጋግሯል።
ይልማ ኃይለሚካኤል
ማንተጋፍቶት ስለሺ
አርያም ተክሌ