መጤና ተዛማች ዝርያዎች (IAS)
ማክሰኞ፣ ሰኔ 2 2001ማስታወቂያ
ግን እንሰሳትም መጤ የሚሆኑበት ጊዜ አለ። ለምሳሌ በእኛዉ አገር በዝዋይ ሐይቅ ከመጀመሪ ይገኝ የነበረዉ የዓሣ ዓይነትና ዛሬ በብዛት ያለዉ አንድ አይደለም። ነባሩን አዲሱ ዝርያ እየበላዉ ቁጥሩን እንዳመናመነዉ እዚያዉ የሚገኙና ከሐይቁ ጋ ብዙ ዘመን የኖሩ ዓሣ አጥማጆች ይናገራሉ። እዚህ ጀርመን አገርም የዉሻና ድመቶችን ዝርያ ሳይቀር ከሌላ አገር አምጥተዉ በማላመድ አራብተዉና አሳድገዉ ሲያበቁ ዛሬ እነዚያ መጤዎቹ ነባሮቹን ዝርያዎች እየጎዱ መሆኑ ማነጋገር ጀምሯል።
ሸዋዬ ለገሠ