መድረክ በአዲስ አበባ ያዘጋጀው ሠልፍ
እሑድ፣ ታኅሣሥ 5 2007ማስታወቂያ
በሠልፉ ላይ የተለያዩ መፈክሮች የተሰሙ ሲሆን፥ ሠልፈኞቹ ገዢው ፓርቲ ከሥልጣን ለመውረድ ፈቃደኛ ስላይደለ ሕዝቡ በምርጫ ከሥልጣን ሊያወርደው ይገባል ማለታቸውም ተዘግቧል። በሠላማዊ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት ላይ እየተኪያሄደ ያለው እስራት እና ወከባ በአስቸኳይ ይቁም የሚል ጥሪም በሰልፉ ላይ ተላልፏል። ባለፈው ሣምንት ሠማያዊ ፓርቲን ጨምሮ የዘጠኙ ፓርቲዎች ሊያኪያሂዱ ያቀዱት ሰልፍ በፖሊስ የድብደባ እና የእስራት ተግባር መደናቀፉ መሰማቱ ይታወሳል። መድረክ ዛሬ ያኪያሄደው ሠልፍ 10 የአቋም መግለጫዎችን በማሰማት ከቀኑ 7 ሠዓት ገደማ መጠናቀቁን ዘጋቢያችን ከአዲስ አበባ ገልጧል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚያብሄር
ልደት አበበ