መውሊድ በኢትዮጵያ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 13 2008ማስታወቂያ
1490 ኛው የነብዩ መሀመድ የልደት በዓል «መውሊድ »ዛሬ በመላ ኢትዮጵያ ተከብሯል ።በዓሉ በተለይ በአዲስ አበባው አንዋር መስጊድ የሃይማኖት አባቶች የእምነቱ ተከታዮች ዲፕሎማቶችና የክብር እንግዶች በተገኙበት ነው የተከበረው ።በስነ ስርዓቱ ላይ ሙስሊሞች በድርቅ የተጎዱ ወገኖችን እንዲያስቡ የሃይማኖት አባቶች ጥሪ አድርገዋል ። ከሃይማኖታዊው አከባበር በተጨማሪ ለበዓሉ አቅም እንደፈቀደ በየቤቱ መብልና መጠጥም ይዘጋጃል ። ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ህብረተሰቡ በዓሉን እንዴት እንደሚያከብር ለመዘገብ አዳማ ይገኛል ። በዚያ የሚኖር አንድ ሴተሰብን አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሀመድ