1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መኢአድ ድርጅቱን ከለቀቁ አመራሮች ጋር መታረቁ

ሐሙስ፣ መጋቢት 12 2011

የድርጅቱ የሥራ ሃላፊዎች ከትናንት በስተያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት በኩርፊያም ይሁን በአቋም ልዩነት ከድርጅቱ የለቀቁ የአመራር አባላት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲመለሱ ተወስኗል። የድርጅቱ መሪዎች ነን ብለው ፍርድ ቤት የከሰሱ ግን በእርቁ አለመካተታቸውንም አስታውቋል።

https://p.dw.com/p/3FQzp
Logo Äthiopien Opposition Partei AEUP

እርቅ በመኢአድ

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት መኢአድ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ጊዜያት ከድርጅቱ ከተለዩ የአመራር አባላት ጋር እርቅ ፈጽሞ በጋራ ለመሥራት መስማማቱን አስታወቀ። የድርጅቱ የሥራ ሃላፊዎች ከትናንት በስተያ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት በኩርፊያም ይሁን በአቋም ልዩነት ከድርጅቱ የለቀቁ የአመራር አባላት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲመለሱ ተወስኗል። የድርጅቱ መሪዎች ነን ብለው ፍርድ ቤት የከሰሱ ግን በእርቁ አለመካተታቸውንም አስታውቋል። ወደ ድርጅቱ ከተመለሱት መካከልም የቀድሞው ሊቀ መንበር አቶ ማሙሸት አማረ ይገኙበታል።  
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር 
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ