1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

መተከል ዞን 80 ሺህ ሰዎች ከጫካ ተመለሱ

ሐሙስ፣ መጋቢት 2 2013

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ሰላም ለማስፈን ስራ የጀመረው የተቀናጀ ግብረ ኃይል ባለፉት ሁለት ወራት ወደ ጫካና ተለያዩ አካባቢዎች ሸሽተው የነበሩ 80ሺ የሚደርሱ የኅብረተሰብ ክፍሎች ወደ ቀየአቸው መመለሳቸውን አስታወቀ፡፡

https://p.dw.com/p/3qV7x
Äthiopien Benishangul Region, Stadt  Metekel
ምስል Negassa Dessakegen/DW

በዞኑ የተፈናሉ ዜጎች ቁጥር 196ሺ መድረሱ ይነገራል

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ሰላም ለማስፈን ስራ የጀመረው የተቀናጀ ግብረ ኃይል ባለፉት ሁለት ወራት ወደ ጫካና ተለያዩ አካባቢዎች ሸሽተው የነበሩ 80ሺ የሚደርሱ የኅብረተሰብ ክፍሎች ወደ ቀየአቸው መመለሳቸውን አስታወቀ፡፡ በዞኑ በተፈጠሩት የጸጥታ ችግሮች ምክንያት ወደ ከተማ ሸሽተው በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያዎች ሚገኙትን በቀጣይ ወደ ቀአቸው መመለስ ስራ እንደሚከናወን የተቀናጀ ግብር ሀይሉ አባል የሆኑት ኮሉኔል አሸናፊ ኢሊ ለዲዳቢሊው ተናግረዋል፡፡ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ በዞኑ የተፈናሉ ዜጎች ቁጥር 196ሺ መድረሱን ዐስታውቋል፡፡

በመተከል ዞን  ከቤት ንብረታቸው  የተፈናቀሉ ዜጎችን ወደ ቀአቸው ለመመለስና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን የተለያዩ የሰላም እና የእርቅ ጉባኤዎች እየተካሄዱ እንደሚገኙ የዞኑ የተቀናጀ ግብረ ሀይል አመልክቷል፡፡ በጉባ ፣ማንዱራ ድባጢ እና ቡሌን ወረዳዎች የሰላም ጉባኤ መካሄዳቸው የግብረ ሀይሉ አባል የሆኑት ኮሎኔል አሸናፊ ዓሊ ለዲዳቢሊው ተናግረዋል፡፡ 164 በሚደርሱ ቀበሌዎችም የሰላም ጉባኤዎች የተካሄዱ ሲሆን  ወደ ጫካ ሸሽተው የነበሩ ዜጎችም ወደ ቀያአቸው እየተመለሱ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡ በዞኑ በተፈጠረው የጸጥታ ችግር ተፈናቅለው በጊዜያዊ መጠለያ ጣቢያ ከሚገኙት በተጨማሪም በርካታ  ዜጎች ወደ ጫካ እና የተለያዩ ስፍራዎች ሽሽተው መቆየታቸውንም አብራርተዋል፡፡  በዞኑ ዘላቂ ሰላምን በማስፋን ሁሉንም ዜጎች ወደ ቀየአቸው ለመመስም  በሁሉም አካባቢዎች የሰላም እና ዕርቅ ጉባኤዎች እንደሚካሄዱም አክለዋል፡፡

ከሳምንት በፊት  በዞኑ በተደረገው የሰላም ጉባኤ ላይ የተሳተፉት ከዳንጉር ወረዳ ተፈናቅለው የነበሩት አቶ ኃይሉ ምትኩ በአካበቢው አሁንም አልፎ አልፎ የሚስተዋዋሉ ጥቃቶች መኖራቸውን የገለጹ ሲሆን  ከሚካሄዱት እርቆችና ጉባኤዎች ጎንለ ለጎንን መንግስት ዘላቂ ሰላም ማስፈን እንዳላበት ሀሳብ አቅርበዋል፡፡ ለተፈናቀሉ ዜጎች የሚቀርቡ የእለት ደራሽ ድጋፋም አነስተኛ መሆኑን በየጊዜ የሚቀርቡ ቅሬታዎች ናቸው፡፡

የቤኒሻጉል ጉሙዝ ክልል የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ በዞኑ የተፈናቀሉ ዜጎ ቁጥር ከ190ሺ በላይ መድረሱን ገልጸው  የወደሙ ቤቶችን መልሶ የመገንባት ስራን እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ የዕለት ደራሽ ድጋፎችም ለማዳረስ በዞኑ የማስተባበርያ ጽ/ቤት ከፍተው አገልግሎት እየሰጠ እንደሚገኝ የኮሚሽኑ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ታሲሳ ተናግረዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የተባበበሩት መንግስታት የስድተኞች መርጃ ድርጅት  በመተከል የሚስተዋለው ግጭት ሸሽተው 7ሺ የሚደርሱ ዜጎች ወደ ሱዳን ብሉ ናይል ግዛት መሻገራቸውን ገልፀዋል።

ነጋሣ ደሳለኝ

ማንተጋፍቶት ስለሺ

አዜብ ታደሰ