ሕገ-ወጥ የተባሉ ቤቶች ፈረሳ በዓዲግራት
ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 1 2011ማስታወቂያ
በዓዲግራት ዙርያ የሚገኙ ቀርሰበርና ማይመሳኖ የተባሉ አካባቢዎች ለአመታት ኑሯቸው ያደረጉ ቅሬታ አቅራቢዎች እንደሚሉት በቅርቡ እየፈረሱ ያሉት መኖርያ ቤቶች ሕጋዊ ሰነድ ያላቸው መሆናቸው ይገልፃሉ፡፡ በ2007 ዓ.ም በአካባቢው የነበሩ ሕጋዊ ሰነድ ያልነበራቸው ቤቶች መፍረሳቸውን የሚገልፁት ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች በወቅቱ ሕጋዊ የተባሉ ቤቶች አሁን ሕጋዊ አይደሉም' ተብሎ ያለ አግባብ ንብረታችን እየወደመ ነው ይላሉ፡፡እስካሁን ከሶስት መቶ በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን የሚገልፁት ነዋሪዎቹ በነባር ይዞታ ላይ የተገነቡ መኖርያዎችንም የማፍረስ ዘመቻው አካል ሆነዋል ይላሉ፡፡
ሚሊዮን ኃይለስላሴ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሐመድ