ሊቢያና የሕክምና ባለሙያዎቹ ተከሳሾች ብይን11 ሐምሌ 1999ረቡዕ፣ ሐምሌ 11 1999የሊብያ ከፍተኛ የፍትህ አካል ከአራት መቶ የሚበልጡ ሊብያውያን ህጻናትን በኤድስ አስተላላፊ ተህዋሲ ሆን ብለው መርዘዋል በሚል የተከሰሱትን አምስት ቡልጋርያውያት ነርሶችንና አንድ ፍልስጤማዊ ዶክተር ላይ ተበይኖ የነበረውን የሞት ቅጣት ወደ ዕድሜ ልክ እስራት ቀየረ። ስድስቱ ተከሳሾች አሁን ወደ ቡልጋርያ መዛወር የሚችሉበት ሁኔታ ሊፈጠርላቸ እንደሚችል ድርድር እንደሚጀመር ተስፋ አድርገዋል።https://p.dw.com/p/E0alአምስቱ ቡልጋርያውያት ነርሶችና ፍልስጤማዊው ዶክተርምስል picture-alliance / dpaማስታወቂያ