ለፖለቲካ እስረኞች የሚጠየቀው ፍትህ
እሑድ፣ ታኅሣሥ 29 2010ማስታወቂያ
በሀገር ውስጥ ከህዝቡ ጠንከር ያሉ ጥያቄዎች የመጡበት የሀገሪቱ መንግሥት ከተቃዋሚዎቹ ጋር ለመደራደር በወሰነበት ጊዜ ከፓርቲዎቹ ከቀረቡ ጥያቄዎች አንዱ የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ የሚለው ነዉ። ይኸው አቤቱታ በበይነ መረብ ሳይቀር የታሰሩትን ሰዎች ስም፣ የታሰሩበትን ምክንያት እና በእስር ላይ የደረሰባቸው በመዘርዘር ትኩረት ለመሳብ ተሞክሯል።የፖለቲካ እስተኞች በሀገሪቱ የሉም የሚለዉ መንግሥት፤ ከሰሞኑ በፖለቲካ ፓርቲ ውስጥ ተሳትፎ ያላቸው እና ሌሎች ግለሰቦች ያላቸዉን ሕጉ በሚፈቅደው መሠረት እንደሚፈታ ጠቁሟል። ዶቼ ቬለ በበይነ መረብ « ፍትህ ለሕሊና እስረኞች» በሚል ዘመቻ ካካሄዱት መካከል ከተወሰኑት ጋር ለፖለቲካ እስረኞች የሚጠየቀው ፍትህ እና መንግሥት የሰጠውን ፍንጭ በተመለከተ ውይይት አካሂዷል። ሙሉ ዉይይቱን ከድምጽ ዘገባዉ ያድምጡ፤
ሸዋዬ ለገሠ