1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች የህዝበ ውሳኔ ዝግጅት መደረጉ

ማክሰኞ፣ መስከረም 18 2014

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ከነገ በስቲያ ሐሙስ ለሚያካሂዱት ህዝበ ውሳኔ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የኢትዮጲያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ ። በቦርዱ የህዝበ ውሳኔ ጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ነጋሳ እንዳሉት ህዝበ ውሳኔን ለማስፈጸም የምርጫ አስፈጻሚዎች የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን ከፍተው ስራ ጀምረዋል ።

https://p.dw.com/p/40ziZ
Äthiopien Referendum
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች የህዝበ ውሳኔ ዝግጅት መደረጉ ተገለጸ

የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ከነገ በስቲያ ሐሙስ ለሚያካሂዱት ህዝበ ውሳኔ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረጉን የኢትዮጲያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ ።

በቦርዱ የህዝበ ውሳኔ ጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አቶ ሙሉጌታ ነጋሳ ዛሬ ለዶቼ ቬለ (DW) እንደገለጹት ህዝበ ውሳኔን ለማስፈጸም የድምፅ መስጫ ቁሳቁሶች ስርጭት የተከናወነ ሲሆን የምርጫ አስፈጻሚዎችም የድምፅ መስጫ ጣቢያዎችን ከፍተው ስራ ጀምረዋል ።

በአዲስ ክልል ለመደራጀት አልያም የደቡብ ክልል አካል ሆኖ ለመቀጠል በቀረቡት ምርጫዎች ዙሪያ የተካሄዱ ቅስቀሳዎች እኩል እድል አላገኙም የሚሉ ቅሬታዎች ይሰማሉ ፣ ለዚህ ምን ምላሽ አላችሁ ? በሚል ከዶቼ ቬለ (DW)  ለቀረበላቸው ጥያቄም << በምርጫ ህጉ መሰረት ሁለቱንም አይነት አማራጭ ሀሳቦችን ለሚያራምዱ ወገኖች አኩል እድል ሰጥተናል ፣ ችግሩ በእድሉ ሳይጠቀሙ መቅረታቸው ነው >> የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

በከፋ ዞን ቦንጋ የሚገኘው ዘጋቢያችን ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ ከስፍራው ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል

ሸዋንግዛው ወጋየሁ 

ታምራት ዲንሳ

አዜብ ታደሰ