1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለዩክሬይን መልሶ ግንባታ ያቀደዉ ስብሰባ

ሰኞ፣ ሰኔ 27 2014

ሩሲያ በዩክሬይን ላይ ጦርነት ከጀመረች ከአራት ወራት ገደማ በኋላ ከአርባ አገሮች የተውጣጡ ልዑካን በሉጋኖ ስዊዘርላንድ ሀገሪቱን መልሶ በመገንባት ላይ መወያየት ጀመሩ። በጦርነት የተመታችዉ ሃገር የዩክሬይን መንግስት ለመልሶ ግንባታው ሂደት ቅድሚያ መስጠት የሚፈልጋቸዉን ነገሮች በስዊዘርላንድ በሚካሄደዉ ዉይይት ላይ ማቅረብ እንደሚፈልግ ተነግሮአል።

https://p.dw.com/p/4DeET
Ukraine-Krieg - Wiederaufbaukonferenz in Lugano
ምስል Fabrice Coffrini/AFP

ሩሲያ በዩክሬይን ላይ ጦርነት ከጀመረች ከአራት ወራት ገደማ በኋላ ከአርባ አገሮች የተውጣጡ ልዑካን ከዚህ ሳምንት ሰኞ ጀምሮ በሉጋኖ ስዊዘርላንድ ሀገሪቱን መልሶ በመገንባት ላይ መወያየት ጀመሩ። በጦርነት የተመታችዉ ሃገር የዩክሬይን መንግስት ለመልሶ ግንባታው ሂደት ቅድሚያ መስጠት የሚፈልጋቸዉን ነገሮች በስዊዘርላንድ በሚካሄደዉ ዉይይት ላይ ማቅረብ እንደሚፈልግ ተነግሮአል። የስብሰባው ዓላማ በተለይ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት በኋላ አውሮጳ እንደገና እንድትገነባ አስተዋጽኦ ባደረገው በማርሻል እቅድ ላይ የተመሠረተ እቅድ ለማዉጣት እንደሆነም ተመልክቶአል። ከዚህ በተጨማሪ ዩክሬን በአገሪቱ ውስጥ የተስፋፋውን ሙስና ለመዋጋት መጠነ ሰፊ ተሃድሶ እንድታደርግ በዚሁ ስብሰባ  ጥሪ እንደሚቀርብ ተገልጿል።

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ