ሙዚቃለ«የኛ» የሚሰጠዉ ርዳታ መቋረጡ2 ጥር 2009ማክሰኞ፣ ጥር 2 2009የብሪታንያ ዓለም አቀፍ የርዳታ ጽ/ቤት «የኛ» ለተሰኘዉ የኢትዮጵያ ሴቶች የሙዚቃ ቡድን የሚሰጠዉን የገንዘብ ርዳታ ማቆሙን አስታዉቋል የሚለዉ ዜና ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ይፋ ከሆነ በኋላ በብሪታንያ ርዕሱን ሽፋን ያልሰጡት ጥቂት የስፖርት ማኅበራዊ መገናኛዎች ብቻ ነበሩ። https://p.dw.com/p/2VaeVምስል A. Getmannማስታወቂያ መንግሥት « ገርል ኢፌክት »ከተሰኘዉና ከኛ ቡድን ጋራ ለሚሰራ 11,8 ሚሊዮን የእንጊሊንዝ ፓዉንድ ከጎርጎረሳዉያኑ 2015 እስከ 2018 ዓ,ም ድረስ ከከፈለ በኋላ ነዉ ርዳታዉን ማቆሙን ያስታወቀዉ። የብሪታንያ ዓለም አቀፍ የርዳታ ጽ/ቤት ድጋፉን ማቋረጡ ለምን ይሆን። ዝርዝሩን የብሪታንያዋ ወኪላችን ልካልናለች። ሃና ደምሴ አዜብ ታደሰ አርያም ተክሌ