ለአፍሪቃዉ እና ለአዉሮጻዉ ህብረት የኤርትራዉያኑ ድርጅት የላከዉ ጥሪ
ዓርብ፣ ሰኔ 4 2002ማስታወቂያ
የኤርትራ መንግስት በዜጎቹ ላይ የሚፈጽመዉን የሰብአዊ መብት ጥሰት እንዲያቆም የበኩላቸዉን እንዲያደርጉ በደብዳቤ የጠየቀ መሆኑ ተመልክቶአል። የኤርትራዉያኑ የሲቢክ ድርጅት ለአዉሮጻዉ ህብረት ኮሚሽን ፕሪዝደንት ሁሴ ማኑኤል ባሮሶ እና ለአፍሪቃዉ ህብረት ሊቀመንበር ዦን ፒንግ ደብዳቤዉን የላከዉ በያዝነዉ ሳምንት መጀመርያ ላይ አዲድ አበባ ላይ ያካሄዱትን የጋራ ስብሰባ ምክንያት በማድረግ ሁለቱም ለአካባቢያቸዉ ችግር ትኩረት እንዲሰጡ ለማሳሰብ ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ ታዉቋል። የደብዳቤዉ ይዘት ምን ይሆን? የብረስልሱ ወኪላችን ገበያዉ ንጉሴ ዘገባ ልኮልናል።
ገበያዉ ንጉሴ፣ አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ