ለአፍሪቃዉያን ባለሙያዎች ዓዉደ ርዕይና ሥልጠና
ረቡዕ፣ ኅዳር 1 2008ማስታወቂያ
ትምህርቱን እየሰጡ የሚገኙት ከተለያዩ ሀገሮች የተዉጣጡ አስራ አንድ ከፍተኛ ባለሙያዎች ናቸዉ። ከኢትዮጵያም የዘርፉን ባለሙያዎች ጨምሮ በአጠቃላይ ከአፍሪቃ 250 ሰልጣኞች አዲስ አበባ በተጀመረዉ ስልጠና ላይ የሚገኙ ሲሆን፣ ስልጠናው በተለይ ለሴቶች ትኩረት መሰጠቱ ተመልክቶአል። ይህ ዓዉደ ርዕይ በዓባይ ፊልም እና ቴሌቭዥን አካዳሚ ዳይሬክተር ፣ አቶ አብርኃም ኃይሌ አነሳሽነት ፣ እንዲሁም፣ በተመድ የትምህርት ሳይንስና የባሕል በ«ዩኔስኮ» እና በተለያዩ የምዕራብ ሀገራት ድጋፍ አዘጋጅነት ነው የሚካሄደው። ዝርዝሩን የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ ኋይለጊዮርጊስ
አዜብ ታደሰ
አርያም ተክሌ