ለአማራ ተፈናቃዮች ርዳታ ተሰጠ
ረቡዕ፣ ግንቦት 14 2011ማስታወቂያ
በአማራ ክልል በተከሰቱ ግጭቶችና ከሌሎች ክልሎች ተፈናቅለዉ አማራ ክልል የሠፈሩ የአካባቢዉ ተወላጆችን መልሶ ለማቋቋም የሚሰጠዉ ርዳታ እንደቀጠለ ነዉ።የክልሉ የአደጋ መከላከልና የምግብ ዋስትና መስሪያ ቤት እንዳስታወቀዉ ለተፈናቃዮቹ መርጃ ከ330 ሚሊዮን በላይ ብር ከተለያዩ ለጋሾች ተረክቧል።በአማራ ክልል በተለያዩ ምክንያቶች የተፈናቀሉ ከ107 ሺሕ በላይ የክልሉ ነዋሪዎች በተለያዩ አካባቢዎች ተጠልለዋል።ከተፈናቃዮቹ መካከል 36 ሺሕ የሚሆኑት ሰሞኑን ወደቀየቻዉ መመለሳቸዉ ተዘግቧል።
ዓለምነዉ መኮንን
ነጋሽ መሐመድ
ተስፋአለም ወልደየስ