ለንደን በጥቃት ማግሥት
ሐሙስ፣ መጋቢት 14 2009ማስታወቂያ
ለንደን ዉስጥ ትናንት በደረሰዉ ጥቃት ለሞቱ ሰዎች ቤተ-ሰቦችና ለተጎዱ ሰዎች የተለያዩ መንግሥታት፤ ድርጅቶችና የፖለቲካ ፓርቲዎች የሐዘን መልዕክት እያስተላለፉ ነዉ።ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት አለዉ የተባለ አንድ ብሪታንያዊ በመኪና እና በጩቤ ባደረሰዉ ጥቃት ሰወስት ሰዎች ገድሎ፤ አርባ ያክል አቁስሏል።እራሱም በፖሊስ በጥይት ተደብድቦ ተገድሏል።እራሱን የኢራቅና የሶሪያ እስላማዊ መንግሥት (ISIS) ብሎ የሚጠራዉ አሸባሪ ቡድን ለጥቃቱ ኃላፊነቱን ወስዷል።ፖሊስ ከግለሰቡ ጋር አባሪ ተባባሪ ያላቸዉን ሰዎች ዛሬ ሲያስር መዋሉ ተዘግቧል።ሥለ ጉዳዩ የለንደኑ ወኪላችንን በሥልክ አነጋግረነዋል።
ድልነሳ ጌታነሕ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ