ለተፈናቀሉ ወገኖች የኢትዮጵያውያን ርዳታ
ረቡዕ፣ ግንቦት 7 2011መፈናቀል እስከመቼ ይቀጥላል የሚለው በአፋጣኘን መልስ ሊያገኝ የሚገባው ጉዳይ ነው ሲል አሳስቧል። ዜጎች «ይህ የኔ ሃገር ነው» የሚለው እምነታቸው እንዲመለስ እና መሰል ችግሮች እንዲቀረፉም በቀጣይ የእርቅ ሥራዎች ላይ ለመሳተፍ ማቀዱን የትብብሩ ፕሬዝዳንት ተናግረዋል።
ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት ላለፉት ስድስት ዓመታት ኢትዮጵያዊያን መብታቸው እንዲከበር ከፍተኛ ሥራ ሲያከናውን እንደቆየ በመጥቀስ በተለይም በመቶ ስዎች የተፈናቀሉበት የጌዴዎ እና የጉጅ ዞኖች ግጭት ባደረሰውን ጥፋት ለተጎዱት ከመላው ዓለም 18 ሽ የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያን ከ31.4 ሚሊዮን ብር በላይ በማዋጣት ቤቶች እንዲገነቡ ፤ መልሰው ወደነበሩበት እንዲመለሱ እና የመቋቋሚያ ገንዘብ እንዲያገኙ ለማድረግ ሙሉ ገንዘቡን ለወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ ዛሬ አስረክቧል። በዚህም ወደ 1710 ቤቶች ይገነባሉ ተብሏል። ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ የተመረጠበት ምክንያትም በስፍራው ሰፊ የሰው ኃይል ያላቸው መሆኑ፤ ልምዳቸውና ከምንም በላይ የሥራ ማስኬጃውን ወደ 5.7 ሚሊዮን ብር ራሱ ድርጅቱ ለመሸፈን ሙሉ በሙሉ በመስማማቱ መሆኑ ተገልጽዋል። ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን ከዚህ በተጨማሪም በጎንደር በተቀሰቀሰው ግጭት መፈናቀልና ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች በዚሁ ዕለት የ3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል።
ሰሎሞን ሙጬ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ