ለሶማልያ አዲስ የገንዘብ ኖት የማሳተም እቅድ1 የካቲት 2008ማክሰኞ፣ የካቲት 1 2008ሶማልያ ውስጥ «ሽሊንግ» የሚባለው የሀገሪቱ የወረቀት ገንዘብ ኖት እጎአ ከ1980 ዓም ወዲህ ታትሞ ወጥቶ አያውቅም። ካለፉት ሶስት ዓመታት ወዲህ በስልጣን ላይ የሚገኙት ከስዊድን የተመለሱት የሀገሪቱ የማዕከላይ ባንክ ዋና አስተዳዳሪ በሺር ኢሳ አሊ አሁን ለሶማልያ አዲስ የገንዘብ ኖት ለማሳተም እንደሚፈልጉ ገልጸዋል።https://p.dw.com/p/1HsAtምስል SIMON MAINA/AFP/Getty Imagesማስታወቂያ[No title]To play this audio please enable JavaScript, and consider upgrading to a web browser that supports HTML5 audio ይህ ለምን አስፈለገ ? በዝውውር ላይ በቂ ገንዘብ ባለመኖሩ ነው ይሆን ወይስ ሌላ ምክንያት አለ? የዚሁ ገና ይፋ ያልሆነው የማዕከላይ ባንክ ዋና አስተዳዳሪ በሺር ኢሳ አሊ እቅድ ዓላማ ታውቋል? የናይሮቢ ወኪላችን ፋሲል ግርማን ስቱድዮ ከመግባታችን በፊት በስልክ በመጀመሪያ የጠየቅሁት ነበር። ፋሲል ግርማ አርያም ተክሌ ሸዋዬ ለገሠ