ለሶማሊያ የሠላም መፍትሄ ከአፍሪቃ ህብረት
ቅዳሜ፣ መጋቢት 19 2001ማስታወቂያ
በጎረቤት ሶማሊያ ለአስራ ስምንት ዓመታት የዘለቀው የርስ በርስ ጦርነት ይህ ነው የተባለ መቋጫ እስካሁን ባለማግኘቱ ብዙዎችን አሳስቧል። ይህ በመሆኑም የአፍሪቃ ህብረት የፀጥታው ምክር ቤት በተደጋጋሚ ባደረገው ስብሰባ አባል ሀገራት የገቡትን ቃል እንዲያከብሩ ጠይቋል። የአፍሪቃ ህብረት የሠላም አስከባሪ ሀይል፤ በተባበሩት መንግስታት እስኪተካ ድረስ እንደሚሰራም ተገልፃል። ይህ በእንዲህ እንዳለም ኡጋንዳ ተጨማሪ የሠላም አስከባሪ ወታደሮችን መላኳ ታውቋል።
ጌታቸው ተድላ
ማንተጋፍቶት ስለሺ