ለስደተኞች አጋርነት ለማሳየት የተደረገ የእግር ጉዞ
ቅዳሜ፣ ግንቦት 3 2011ማስታወቂያ
የፈረንሳይዋ የድንበር ከተማ ካሌ የተሻለ ህይወትን ፍለጋ ወደ እንግሊዝ ለመሻገር ለሚፈልጉ ስደተኞች እንደ መቆያ ጣቢያ ማገልገል ከጀመረች ዓመታት ተቆጥረዋል። የፈረንሳይ መንግስት ስደተኞቹ በየቁጥቋጦው እና ሰወር ያሉ ቦታዎች በየጊዜው የሚመስርቷቸውን መቆያ ሰፈሮች እየተከታተለ ቢያፈርስም ወደዚያ የሚጓዙ ስደተኞችን ግን ማስቆም አልቻለም። የአውሮፓ ሀገራት እነዚህን ስደተኞች በአግባቡ እና ክብራቸውን በጠበቀ መልክ እንዲያስተናግዱ የጠየቁ ሰዎች ከጣሊያን የድንበር ከተማ እስከ ካሌ ድረስ የእግር ጉዞ አድርገዋል።
የፓሪሷ ወኪላችን ሃይማኖት ጥሩነህ የጉዞውን አስተባባሪዎች እና ተሳታፊዎች አነጋግራ ያጠናቀረችውን ዘገባ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።
ሃይማኖት ጥሩነህ
ተስፋለም ወልደየስ