ለሰላም ጥረት የሴቶች ተሳትፎ
ማክሰኞ፣ ሰኔ 2 2001ማስታወቂያ
ግጭቶችን በመከላከልና ቀውሶችን በማስወገድ ስራ ላይ የተሰማሩ ሰራተኞች እና ከፍተኛ ባለሞያዎች ፖሊሲ አውጭዎችና ምሁራን እንዲሁም የሲቪክና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ተወካዮች የሚካፈሉበት ይህን መሰሉ ስብሰባ በኮሚሽኑ አማካይነት ሲካሄድ የአሁኑ ሶሶተኛው ነው ። አንድ ሺህ ተጋባዥች በተገኙበት በዘንድሮው ስብሰባ ግጭቶችን በመፍታት እና ሰላም በማውረድ ጥረት ውስጥ የሴቶችና የሌሎች የህብረተሰብ ክፍሎች ቀጥተኛ ተሳትፎ ወሳኝነት ውይይት ተካሂዶበታል ። ገበያው ንጉሴ ከብራሰልስ
ገበያው ንጉሴ /ሂሩት መለሰ /ሸዋዬ ለገሠ