ለመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም ፤ የጋራ ጸሎት በቫቲካን--ዩክሬንና ጊዜያዊው ሁኔታ--- 2 ሰኔ 2006ሰኞ፣ ሰኔ 2 2006በዩናይትድ ስቴትስ ተነሳሽነት የመካከለኛው ምሥራቅ የመጨረሻ ዙር ድርድር ከከሸፈ ከሳምንትታ ወዲህ ፤ የሮማ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍርንሲስ፤ በቅርቡ መካከለኛውን ምሥራቅ ሲጎበኙ ያነጋገሯቸውና የጋበዟቸው የእሥራኤል ፕሬዚዳንትhttps://p.dw.com/p/1CF55ምስል Reutersማስታወቂያ ሺሞን ፔሬስና የፍልስጤማውያን ፕሬዚድንት ማህሙድ አባስ፣ ትናንት በቫቲካን የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች ፤ የክርስቲያን ሙስሊምና ይሁዲ ሃይማኖት ሰዎቻ በጋራ በመሩት ሥርዓተ ጸሎት ተሳትፈዋል። ለመካከለኛው ምሥራቅ ሰላም ስለተካሄደው ሥርዓተ ጸሎትና ስለተሰጠው አስተያየት የሮማው ዘጋቢአችን ተኽለዝጊ ገ/የሱስ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።