ህፃናትና ቋንቋ በባዕድ ሀገር
እሑድ፣ የካቲት 15 2001ማስታወቂያ
ቓንቓ አንድ ማህበረሰብ ማንነቱን፣ እሴቱንና ባህሉን የሚጠብቅበት ቁልፍ መሳሪያው ነው። ቓንቓ ከምንም በላይ ደግሞ እርስ በርስ ለመግባባት ወሳኝ ነገር መሆኑ ለማንም ግልፅ ነው። በውጭው ዓለም የሚኖረው ኢትዮጵያዊ ከእለት እለት ቁጥሩ እየተበራከተ ከመሄዱ የተነሳ ስፍር ቁጥር የለውም ማለት ይቻላል። ታዲያ ለመሆኑ ለዘመናት ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ እኛ ዘንድ የደረሰውን ቓንቓችንን፤ ሀገራቸውን በቅጡ ለማያውቁና በባዕድ ሀገራት ለተወለዱ ልጆቻችን የምናቀብልን ስንቶቻችን እንሆን? ለዛሬ እዚህ ጀርመን ሀገር የአንድ ህጻን ኢትዮጵያዊ በዓል ላይ የተሰባሰቡ ህጻናትና ወላጆቻቸውን እናገኛለን።