1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ህገ ወጡ የኤደን ባህረ ሰላጤ ጉዞ እና ያስከተለዉ ችግር

ሰኞ፣ መጋቢት 17 1999

አንዳንድ ሶማልያዉያን እና ኢትዮጽያዉያን ወደ የመን ለመግባት በሚያደርጉት ህገ ወጥ ጉዞ በርካቶች ህይወታቸዉን እያጡ እንደሆነ የተ.መ.ድ የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን አስታዉቋል

https://p.dw.com/p/E0Yc
የአፍሪቃ ቀንድ
የአፍሪቃ ቀንድምስል AP

ባለፈዉ ሳምንት መጨረሻ ላይ ኤደን ባህረ ሰላጤ በትናንሽ ጀልባዎች ለማቋረጥ ለህገ ወጥ ግለሰቦች ገንዘብ በመክፈል ሙከራ ካደረጉት መካከል በትንሹ የ28 ግለሰቦች ሪሳ መኘቱ ተዘግቦአል። ህገ ወጥ መንገድ ባህሩን በጀልባ የሚያሻግሩት ግለሰቦች ሶማልያዉያን መሆናቸዉም ታዉቋል። ግለሰቦቹ ገንዘብ በመቀበል በጀልባ ካሳፈሩ በኳላ፣ ተሳፋሪዎቹን በሰላ ቢላ እና በብረት ዱላ በመደብደብ ባህር ዉስጥ እንዲገቡ እንደሚያስገድዱ UNHCR የቃል አቀባይ ለዛሪ ለዶቸ ቬለ በሰጡት ቃለ ምልልስ ገልጸዋል። በያዝነዉ አመት ብቻ የኤደን ባህረ ሰላጤን ለማቋረጥ የሞከሩ ቢያንስ 500 ግለሰቦች ህይወታቸዉን አጥተዋል 300 ያህል ደግሞ የደረሱበት አይታወቅም።