ሀና ወንድምስሻ
ሰኞ፣ ጥቅምት 7 2009ማስታወቂያ
ሀና ወንድምስሻ ጀርመን የምትኖር ባለትዳርና የሁለት ልጆች እናት ናት ። ኑሮዋን እዚህ ጀርመን ካደረገች 5 ዓመት አስቆጠረች ። ኢትዮጵያ እያለች በጋዜጠኝነት ትሰራ ነበር ። ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ግጥሞቿን አንብባ ልብ ወለዶችዋን እና እወነተኛ ታሪኮቿን ተርካ እና አቀናብራ ዩቱብ እንዲሁም ፌስቡክ ላይ ታወጣለች ። ሀና እንደምትለው በአሁኑ ጊዜ የፌስቡክ ተከታዮቿ ቁጥር ከፍተኛ ነው ። ይኽም ደግሞ ይበልጥ እንድትፅፍ እያበረታታት ነው ።ተወልዳ ያደገችው የአንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቷንም የተከታተለችው ከአዲስ አበባ 180 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው በመራቤቴ እና በዓለም ከተማ ነው ። የስነፅሁፍ ዝንባሌዋን ለማዳበር ከረዷት ውስጥ አስተማሪየ ትልቁን ስፍራ ይይዛሉ ትላላለች ።ሙሉ ዝግጅቱን የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ያዳምጡ
ኂሩት መለሰ