1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፖየቲካ፤ የጀርመኑ ዓለም አቀፍ የሥነ-ጽሑፍ ፊስቲቫል

ቅዳሜ፣ ግንቦት 6 2014

መድረኩ ዓለም አቀፋዊ በተለያዩ ቋንቋዎች በአንድ ርዕስ ስር የሥነ-ጽሑፍ እና የሥነ-ግጥም ክህሎት የሚታይበት ነዉ። አብዛኛዉን ጊዜ መድረኩ ከአስር የተለያዩ ሃገራት የመጡ የኪነ-ጥበብ ሰዎች የሚሳተፉበት ነዉ። በዚህ ዓመት መድረኩን ያዘጋጀሁት እኔ ነኝ ። የዚህ ዓመት ርዕሳችን የድምፅ መረጃዎችን በማህደር ማስቀመጥ ይላል።

https://p.dw.com/p/4BBbs
Deutschland Köln | Poetica 2022 | Lesung mit Mihret Kebede & Chill Cecilia Vicuna
ምስል Mario Brand

በዓለም አቀፍ መድረክ መሳተፍ ሀገርን ማስተዋወቅ ነዉ

ገጣሚ ምህረት ከበደ በጀርመን ኮለኝ ከተማ ለአንድ ሳምንት በተካሄደዉ ዓለም አቀፍ የሥነ-ጽሑፍ ፊስቲቫል መዝግያ ላይ «የፀጥታ ወግ » የተሰኘዉን ግጥሟን በመድረክ ስታቀርብ በአዳራሹ ከነበሩት ተመልካቾች ደማቅ ጭብጨባን ነበር የተቸረችዉ። ምንም እንኳ ጥበበኛዋ ኢትዮጵያዊት ግጥሟን  በአማርኛ ቋንቋ ያቀረበች ቢሆንም ፤ ያቀረበችዉ ግጥም ምህረት ወደ መድረክ ከመዉጣትዋ በፊት ትርጉሙን በጀርመንኛ ቋንቋም ያቀረበዉ የሞያዋ ባልደረበዋ ነበር።  ገጣሚ ምህረት ከበደ የዛሬ አስራ አራት ዓመት ገደማ አዲስ አበባ ላይ የጀመረዉን የግጥም መድረክ «ጦብያ ግጥምን በጃዝን»  ከመሰረቱት ወጣቶች መካከል አንድዋ መሆንዋ ይታወቃል። በሥነ ጥበቡ ዓለም ኢትዮጵያ ዉስጥ የምትታወቀዉ ምህረት ከበደ ከዚህ በፊት ከየሌሎች ኢትዮጵያዉያን ገጣሚዎች ስራን ይዛ በአማርኛ እና በጀርመንኛ «ዋክስ ኤንድ ጎልድ» «ሰምና ወርቅ» የተሰኘ የግጥም መድበልን አሳትማለች። በጀርመን በርሊን መዲና ላይ በነበረ የግጥም በጃዝ ዝግጅት ላይ ሥነ-ግጥሞችዋን አቅርባም ነበር። ምህረት ከበደ ባለፈዉ ሳምንት በጀርመን ኮለኝ ከተማ ላይ በተካሄደዉ በዓለም አቀፍ የሥነ-ጽሑፍ ፊስቲቫል ላይ እንዴት እንደተጋበዘች ጠይቀናት ነበር።

Poetica | Poesie Veranstaltung der Universität Köln und der Deutschen Akademie für Sprache und Dichtung
ምስል Silviu Guiman/Poetica
Poetica | Poesie Veranstaltung der Universität Köln und der Deutschen Akademie für Sprache und Dichtung
ምስል Silviu Guiman/Poetica

በጀርመን ኮለኝ ከተማ በተካሄደዉ በዓለም አቀፉ የሥነ-ግጥም ፌስቲቫል ላይ ከኢትዮጵያዊትዋ ገጣሚ ምህረት ከበደን ጨምሮ ከብሪታንያ ከፈረንሳይ ከቺሊ ከቤላሩስያ ከሩስያ ከቻይና ከጀርመን የመጡ ገጣምያን ተሳትፈዉበታል። ሁሉም ገጣምያን ግጥሞቻቸዉን ያቀረቡት በትዉልድ ሃገራቸዉ ቋንቋ ቢሆንም፤ ግጥሞቻቸዉ ለተመልካች በጀርመንና ተተርጉሞ በግጥም መልክ በመድረክ ላይ ለተመልካቾች ቀርቦአል። በፊስቲቫሉ ላይ ሥነ-ግጥም፤ መነባንብ፤ ትያትር እንዲሁም የተለያዩ ድምፆች እና በተለያዩ የብርሃን ቀለም ድምቀቶች የታጀበ ነበር።  

የዝግጅት ክፍላችን በተገኘበት በፊስቲቫሉ የመዝግያ ሥነ-ስርዓት ላይ ገጣሚ ምህረት ከበደ ያቀረበችዉ «የፀጥታ ወግ» የተሰኘዉ ሥነ-ግጥምዋ በዚህ ዝግጅት ላይ ተካቶአል።  

በጀርመን ኮለኝ ከተማ ለአንድ ሳምንት የተካሄደዉ እና ባለፈዉ ሳምንት ቅዳሜ ሚያዝያ 28 ቀን 2014 ዓ.ም ስለተጠናቀቀዉ ስለዓለምአቀፍ የሥነ-ጽሑፍ ፊስቲቫል የጠየቅናቸዉ የመድረኩ አዘጋጅ ጀርመናዊት ዩልያና ዎልፍ፤ ፖየቲካ በመባል የሚታወቀዉ እና በኮለኝ ዩንቨርስቲ እና በዳርም ሽታት ከተማ በሚገኘዉ የቋንቋ የሥነ-ግጥም እና የሥነ-ጽሑፍ አካዳሚ የተመሰረተዉ ዓመታዊ ዝግጅት መካሄድ የጀመረዉ ከጎርጎረሳዉያኑ 2015 ዓም ጀምሮ እንደሆን ገልፀዋል። መድረኩ ዓለም አቀፍ የሥነ-ጽሑፍ ክህሎት እዉቀት ልዉዉጥ የሚደረግበት እንደሆነም ተናግረዋል።

Deutschland Köln | Poetica 2022 | Lesung mit Mihret Kebede & Chill Cecilia Vicuna

«መድረኩ ዓለም አቀፋዊ በተለያዩ ቋንቋዎች በአንድ ርዕስ ስር የሥነ-ጽሑፍ እና የሥነ-ግጥም ክህሎት የሚታይበት ነዉ። አብዛኛዉን ጊዜ መድረኩ ከአስር የተለያዩ ሃገራት  የመጡ የኪነ-ጥበብ ሰዎች የሚሳተፉበት ነዉ። በዚህ ዓመት መድረኩን ያዘጋጀሁት እኔ ነኝ ። የዚህ ዓመት ርዕሳችን የድምፅ መረጃዎችን በማህደር ማስቀመጥ ይላል። ሥነ-ግጥም በድምፅ በቅላፄ እንዴትነት፤ እነዚህን ክህሎቶች በማህደር እንዴት እናስቀምጥ፤ ብሎም የምናስቀምጣቸዉ እንዲህ አይነት ማህደሮቻችን እንዴት ጥቅም ላይ ማዋል ይኖርብናል የሚለዉንም የምናይበት ነዉ።  በዚህ መድረክ ከተለያዩ ሃገራት የመጡ የሥነ-ግጥም ባለሞያዎች ሥነ-ግጥሞቻቸዉ ምን አይነት ቅላፄ እንዳላቸዉ የሚለዉን ጨምሮ ሌሎችንም ጥያቄዎችን በጋራ አይተናል። 

Mihret Kebede Äthiopien Künstlerin
ምስል Martha Tadesse/DW
Poetica | Poesie Veranstaltung der Universität Köln und der Deutschen Akademie für Sprache und Dichtung
ምስል Azeb-Tadesse Hahn/DW

የዘንድሮ የጀርመንዋ ከተማ ኮለኝ የዓለም አቀፍ የሥነ-ጽሑፍ ፊስቲቫል ተካፋዮች ያቀረቡት ሥነ-ግጥም መነባንብ በአንድ ላይ በየቋንቋቸዉ እና ከነትርጉሙ በአንድ መጽሐፍ ታትሞ ለአንባብያን ቀርብዋል።

ሙሉዉን ቅንብር የድምፅ ማድመጫ ማዕቀፉን በመጫን እንዲከታተሉ እንጋብዛለን።

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ