1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ፈረንሳይ፣ ተቃዉሞ እና አድማ

ሐሙስ፣ ኅዳር 27 2011

በሕዝባዊዉ ተቃዉሞ አድማ ምክንያት የቀድሞ አቋሙን የለወጠዉ የፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮ መንግስት በነዳጅ ዘይት ዋጋ ላይ የተደረገዉን የዋጋ ጭማሪ ለስድስት ወር በሥራ ላይ እንዳይወል አግዷል

https://p.dw.com/p/39baz
Frankreich Gelbwesten-Protest in Paris
ምስል Getty Images/AFP/G. van der Hassel

አድማዉ የሐገሪቱን ምጣኔ ሐብት እያሽመደመደዉ ነዉ

የፈረንሳይ መንግስት በነዳጅ ዘይት ላይ ያደረገዉን የዋጋ ጭማሪ በመቃወም በተለያዩ  ከተሞች የተደረገ እና የሚደረገዉ የአደባባይ ሰልፍ እና አድማ የሐገሪቱን ምጣኔ ሐብት እያሽመደመደዉ ነዉ።«ቢጫ ሰደርያ » የሚባሉት አድመኞች ከፀጥታ አስከባሪዎች ጋር በገጠሙት ግጭት የሰዉ ሕይወት ጠፍቷል፤ ሐብት ንብረትም ወድሟል። በሕዝባዊዉ ተቃዉሞ አድማ ምክንያት የቀድሞ አቋሙን የለወጠዉ የፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮ መንግስት በነዳጅ ዘይት ዋጋ ላይ የተደረገዉን የዋጋ ጭማሪ ለስድስት ወር በሥራ ላይ እንዳይወል አግዷል። የተቃዉሞ ሰልፉ አስተባባሪዎች ግን ተጨማሪ ተቃዉሞ እንዲደረግ እየጠሩ ነዉ።አንዳድ ፖለቲከኞች ደግሞ መንግስት አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲደነግግ እየገፋፉ ነዉ።

ኃይማኖት ጥሩነሕ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ