ጾታ እና የመገናኛ ብዙኃን ዘገባ
ረቡዕ፣ ታኅሣሥ 24 2011ማስታወቂያ
መገናኛ ብዙኃን ሴቶችን በመረጃ ምንጭነት በመጠቀምም ሆነ በአጠቃላይ የስርዓተ ጾታ እኩልነትን በማረጋገጥ የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ ተጠየቀ። ጥያቄው የቀረበው የፌደራል ብሮድካስቲንግ ባለሥልጣን ያዘጋጀውን የሥርዓተ ጾታና የመገናኛ ብዙሀን ዘገባ ማኑዋል ለማዳበር ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡ የመገናኛ ብዙሀን ኃላፊዎች እና ጋዜጠኞች በተሳተፉበት ዐውደ-ጥናት ላይ ነው። በዐውደ ጥናቱ መገናኛ ብዙኃን በማኅበረሰቡ ውስጥ ያሉትን የተዛቡ የስርዓተ ጾታ አመለካከቶችን ለመቀየር የሚያስችላቸውን አቅማቸውን እንዲጠቀሙበትም ጥሪ ተላልፏል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ማንተጋፍቶት ስለሺ