1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጥበብ በጠርሙስ  

እሑድ፣ ጥቅምት 25 2011

ጠባብ በሆነው የጠርሙስ የአፍ ቀዳዳ ቀጭን ረጅም ብረት በማስገባት የተለያዩ ቅርጾችን ይሰራል። አድካሚ ትዕግስትን የሚጠይቅ ጥንቃቄ የተሞላበት ጥበብ ነው። ለሚያየው ያስደንቃል። እንዴትና በምን ሁኔታ ተሰራ ብለው ይገረማሉ። አለፍ ሲሉም ይመራመራሉ። 

https://p.dw.com/p/37ccM
Äthiopien Glasmalerei Dawit Tefera
ምስል privat

ጥበብ በጠርሙስ፦አድካሚና ጥንቃቄ የተሞላበት ጥበብ ነው

ዳዊት ተፈራ የጠርሙስ ጥበብ ባለሙያ ነው። በፊልም ላይ የመርከቦችን ቅርጽ በማየት ለመስራት እንደተነሳሳ ይናገራል። በረጅም ብረት በመታገዝ ወደ ጠርሙሱ የውስጠኛው ክፍል የሚገጥማቸውን ዕቃዎች ያስገባል። በተፈለገበት ቦታ በማስቀመጥ ቅርጹን ነፍስ ይዘራበታል። ጥንቃቄ የሚጠይቅና በትዕግስት የሚሰራ እርጋታና ጥሞናን ሰጥቶ የሚሰራ ነው። እያንዳንዱ ጥንቃቄ የጎደላት እንቅስቃሴ ስራውን እንዲበላሽ ያደርገዋል ይላል ዳዊት። የወዳደቁ ጥሬ ዕቃዎችም ይጠቀማል። ጨርቅ፣ ፌስታል፣ እንጨት፣ ክር፣ ጅብሰም፣ ብረት የመሳሰሉት የጥበቡ መጠቀሚያዎቹ ናቸው። ጥበቡ በብዙ መንገድ ይገለጻል። ሁሉም ነገር ከአርት ተነስቶ ነው ወደ እውነታው የሚመጣው ይለናል። አንድ የጠርሙስ ውስጥ ጥበብን ቅርጽ ለመስራት እንደቅርጹ ሁኔታ የሚወሰን ቢሆንም እስከአንድ ወር እንደሚፈጅበት ገልጾአል። ጥበብን ለነፍሴ እንደሚሏት የጥበብ ሰዎች ይሰራል እንጂ በሙያው የካሜራ ባለሙያ ነው።
በዚህ ጥበብ ጠርሙሶች ለእርሱ መልዕክት ያስተላልፍልኛል ይላል። በእኔ በኩል ጥረት እያደረኩ ነው። እየሰራሁ ለህዝብ እያቀረብኩ ነው። ሌሎችም እንዲሰሩ አድርጊያለሁ። ተጨማሪ ሌላ ስራ ካልተሰራ በዚህ የአርት ሙያ መኖር አስቸጋሪ እንደሚሆን ይናገራል። አቶ ቅዱስ ማርቆስ ይባላሉ። የጥበብ አድናቂ ናቸው።ጥበብን ከማድነቅ ቀድሞ እንዴት ሰራው የሚለው ነገር የበለጠ አመራምሯቸዋል። ከውጭ ሆኖ ለመስራት የሚከብድ ያሉትን የዳዊትን ትዕግስቱንም ጥበቡንም አድንቀዋል። እስከዛሬ ካዩትም የዳዊት የተለየባቸው እንደሆነ በጠርሙስ ቀዳዳ እየገጣጠመ መስራት መቻል ከመደነቅም አልፈው አስጨናቂ እንደሆነባቸው ተናግረዋል። እያሱ ሲሳይ ሰአሊና የስዕል አስተማሪም ነው። ሰዎች አርትን ይገልጽልኛል በሚሉት ሀሳባቸውን ይገልጻሉ። እሱ የሚጠቀምበት መንገድ ሀሳቡን የሚገልጽለት ሆኖ ስላገኘው ተጠቅሞበታል። የጥበብ አሰራር ዘዴውም እንደወደደው፤ ጥሞናን የሚፈልግ፣ አድካሚ እና ጥንቃቄ የሚፈልግ ሆኖ አግኝቶታል።
የጠርሙስ ውስጥ ጥበብ በብዙዎች ዘንድ ያልታየና ያልተሰራበት ነው። ፈጠራው ለረጅም ጊዜ ትኩረት ሰጥቶ መስራት የሚፈልግ ስራ ነው። የበለጠ የሚያግዘው ሰው ቢያገኝ ጥበብን ሊያሳድገው ይችላል እንደባለሙያው እያሱ አስተያየት።

Äthiopien Glasmalerei Dawit Tefera
ምስል Dawit Tefera
Äthiopien Glasmalerei Dawit Tefera
ምስል Dawit Tefera

ነጃት ኢብራሂም 
አዜብ ታደሰ