1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ስለ ጥቃትና ግጭቱ የዶ/ር ነገሪ ሌንጮ ምላሽ

ማክሰኞ፣ መስከረም 8 2011

በቡራዩና በአከባቢዋ ነዋሪዎች መካከል ግጭት የቀሰቀሱት «99 አባላትን የያዙ እና የፖለቲካ አላማ ያላቸዉ» ቡድኖች ናቸዉ ሲሉ የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ለ«DW» ተናገሩ። ከእነዚህም ዉስጥ ስድስት ሰዎች ሲያዙ ቀሪዎቹን ለማያዝ ፖሊስ እያሰሰ መሆኑን  ዶክተር ነገሪ አስታዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/357H2
Äthiopien Proteste | Dr. Negeri Lench
ምስል DW/M. Yonas Bula

ስድስት ሰዎች ተይዘዋል ቀሪዎቹን ለማያዝ ፖሊስ እየሰሰ ነዉ

በቡራዩና በአከባቢዋ ነዋሪዎች መካከል ግጭት የቀሰቀሱት «99 አባላትን የያዙ እና የፖለቲካ አላማ ያላቸዉ» ቡድኖች ናቸዉ ሲሉ የኦሮሚያ ክልል የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ፅፈት/ቤት ኃላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ለ«DW» ተናገሩ። ከእነዚህም ዉስጥ ስድስት ሰዎች ሲያዙ ቀሪዎቹን ለማያዝ ፖሊስ እየሰሰ መሆኑን ዶክተር ነገሪ አስታዉቀዋል። የተያዙት ስድስት ግለሰቦች ሦስት ክላሽንኮቭ፣ ስምንት ሽጉጥ፣ ሁለት መኪና፣ ስምንት ሚሊዮን ብር የያዘ የባንክ ሒሳብ፣ የባንክና የመሬት አስተዳደር የሐሰት ማህተምና የሐሰት ገንዘብ እንደተገኘባቸዉም ገልፀዋል።

እነዚህ ግለሰቦች በቅርቡ ከዉጭ የገቡ የፖለትካ ፓርቲዎችን «በማስመሰል» ጥቃት ፈፅመዋል ሲሉ ዶ/ር ነገሪ አክለዋል። እነዚሕ ቡድኖች በቻሉት መንገድ «የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ የሚፈልግ አካል መጠቀምያም» ናቸዉም ብለዋል። ፖሊስ በአፋጣኝ ርምጃ ባይወስድ ኖሮ ቡድኑ ባቀደዉ መሰረት «የከፋ ጉዳት ይደርስ ነበር» ሲሉ የኮሙኒኬሼን ጉዳዮች ፅፈት/ቤት ኃላፊ ዶክተር ነገሪ ሌንጮ ተናግረዋል። መርጋ ዮናስ ዶክተር ነገሪ ሌንጮን አነጋግሮአቸዋል፤ የድምጽ ማዕቀፉን ተጭነው ያድምጡ።   

መርጋ ዮናስ 

ነጋሽ መሃመድ