ጥምቀትና ቱሪዝም
ረቡዕ፣ ጥር 10 2015ማስታወቂያ
በዬኔስኮ በማይዳሰስ እሴትነት የተመዘገበው ጥምቀት በድምቀት ከሚከበርባቸው ስፍራዎች አንዱ የባቱ ከተማ ነው። በባቱ ከተማ በቀድሞ አጠራሯ ዝዋይ የደመበል ሐይቅ ላይ ከሚገኙ ገዳማት ታቦታት ወጥተው በሐይቁ ላይ የሚከበረው ጥምቀት የተለየ ድባብ እንዳለው በዚያ የሚገኘው ወኪላችን ስዩም ጌቱ ዘግቧል። ዶቼቬለ በባቱ ከተማ ያነጋገራቸው የኦሮምያ ክልል የቱሪዝም መስሪያ ቤት ሃላፊ የጥምቀት በዓል አከባበርን ሃይማኖታዊ እና ባህላዊ እሴቶችን ለቱሪዝም ለመጠቀም መሰረተ ልማቶችን ማሟላት ላይ ትኩረት ሊደረግ ይገባል ብለዋል፡፡
ሥዩም ጌቱ
ኂሩት መለሰ