1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያካሄዱት ውይይት 

ሰኞ፣ ሰኔ 21 2013

ምርጫ ቦርድ ውጤት እስኪያሳውቅ መጠበቅና ውጤቱን በፀጋ መቀበል እንደሚገባም ተናግረዋል ብለዋል ።ውጤት ከታወቀ በኋላ ሕገ መንግሥቱ አብላጫ ድምፅ ያገኘው ፓርቲ መንግሥት እንደሚመሰርት ቢደነግግም ሙያዊ ድጋፍ የሚያደርጉት በመንግሥት ምስረታው ውስጥ ግምት እና ቦታ እንዲኖራቸው እንደሚያደርጉ መናገራቸውንምልፀዋልል።

https://p.dw.com/p/3vhsK
Äthiopien Premierminister Abiy Ahmed Parlament
ምስል Yohannes Gebireegziabher/DW

ጠ/ሚ ዐቢይ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ያካሄዱት ውይይት 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጳጉሜን አንድ ቀን የሚደረገው ምርጫ ከሰኔ 14 ቱ የተሻለ ሆኖ እንዲካሄድ መንግሥት ጥረት ያደርጋል ሲሉ ዛሬ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ኃላፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት መናገራቸው ተገለፀ።ምርጫ ቦርድ የምርጫ ውጤት እስኪያሳውቅ መጠበቅና ውጤቱን በፀጋ መቀበል እንደሚገባም ተናግረዋል ብለዋል ዶቼቬለ ያነጋገራቸው በውይይቱ የተሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሃላፊዎች ።ውጤት ከታወቀ በኋላ ሕገ መንግሥቱ አብላጫ ድምፅ ያገኘው ፓርቲ መንግሥት እንደሚመሰርት ቢደነግግም ሙያዊ ድጋፍ የሚያደርጉት በመንግሥት ምስረታው ውስጥ ግምት እና ቦታ እንዲኖራቸው እንደሚያደርጉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ መናገራቸውን የፓርቲ ኃላፊዎች ገልፀዋልል። ሀገሪቱ የፀጥታ ሁኔታም ሌላው የመነጋገሪያ ጉዳይ እንደነበርም ፓርቲዎቹ አስታውቀዋል። ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ