1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ግጭት የጋረደው ድርቅና የርሃብ አደጋ

እሑድ፣ ታኅሣሥ 7 2016

በትግራይ ክልል ሁለት ሚሊየን ሕዝብ ለርሀብ መጋለጡን ተገልጿል። በክልሉ የአፅቢ ወረዳ አስተዳደር በወረዳዋ ብቻ ባለፉት ሶስት ወራት 111 ሰዎች በረሃብ መሞታቸውን ለዶቼቬለ ገልጿል። አማራ ክልል በተለይ ሰሜን ጎንደር ዞን በስድስት ወረዳዎች 83 ቀበሌዎች ላይ ድርቅ መከሰቱን የአደጋ መከላከል ባለሥልጣን ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/4aEI6
ፎቶ፤ ትግራይ ክልል በድርቅ የተጎዳው አካባቢ
በሰሜን ኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች ድርቅ እና ረሃብ የበርካቶችን ሕይወት እየቀጠፈ እንደሚገኝ እየተገለጸ ነው። ፎቶ፤ ትግራይ ክልል በድርቅ የተጎዳው አካባቢምስል Million Hailesilassie/DW

ግጭት የጋረደው ድርቅና የርሃብ አደጋ

ኢትዮጵያን በዓለም መድረክ በረሀብ ካስጠራው የ1960ዎቹ ዓም ድርቅ ወዲህ የዝናብ መታጣት ያስከተላቸው የረሀብ ክስተቶች ዓመታትን እያሰለሱ ተከስተዋል። ምንም እንኳን የድርቅ እና የርሃቡ ክስተት በኢትዮጵያ ከ50 ዓመታት በላይ ቢያስቆጥርም ዘላቂ መፍትሄ ባለመፈለጉ አሁንም ዜጎች ለረሀብ ተጋልጠው የድረሱልን ድምፅ እያሰሙ ነው። ሰሜን ኢትዮጵያ ላይ የድርቅ የርሀብ ወሬ መሰማት ከጀመረ ሰነባበተ። በጦርነት ድባብ በከረመችው ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር መረጃ በአሁኑ ወቅት በክልሉ 2 ሚልዮን ዜጎች ለረሃብ ተጋልጠዋል። ቀደም ሲል ለሁለት ዓመታት በዘለቀው ጦርነት፤ አሁን ደግሞ በመንግሥት እና በፋኖ ኃይሎች መካከል በሚካሄደው ውጊያ በሚደቀው አማራ ክልልም የድርቅና ረሀብ አደጋው በርካቶችን ለችግር መዳረጉ እየተነገረ ነው። ይኽ ብቻም አይደለም፤ በየቦታው የሚገኙ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችም የሰብአዊ እርዳታ ለማግኘት መቸገራቸን ይገልጻሉ። የእርሻ ምርት ተትረፍርፎባት ስንዴ ወደ ውጪ ለመላክ መብቃቷ እየተወራ፤ ስለቅንጡ ፕሮጀክቶችም ብዙ እየተነገረ ባለበት ሀገር በግጭት ድባብ ውስጥ የተከለለው ርሀብ እያደረሰ ያለው ጉዳት ትኩረት ያገኘ አይመስልም። የረድኤት ድርጅቶች እጃቸውን መሰብሰባቸውም ለረሀብ አደጋው መባባስ ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው የሚገልጹም አሉ። ለድርቅና ረሀቡ መፍትሄ ጠፋ? በረሀብ ለሚሰቃዩትስ እንዴት ይደረስ? «ግጭት የጋረደው ድርቅና የርሃብ አደጋ በኢትዮጵያ» የዶቼ ቬለ የዚህ ሳምንት መወያያ ርዕሳችን ነው። በውይይቱየሚከተሉት ነጥቦች ተነስተዋል።

 ሸዋዬ ለገሠ