1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ መለቀቁን ተናገረ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 2 2014

በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች እሁድ ሚያዚያ 23 ቀን፣2014 ዓ.ም በቁጥጥር ሥር የነበረዉ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ለዘጠኝ ቀናት የነበረበት አድራሻ ጠፍቶ ቆይቶ ትናንት እራሱን ቤቱ ደጃፍ ላይ እንዳገኘ ገለፀ። በጤንነቱ ላይ ምንም ነገር እንዳልደረሰም ባስተላለፈዉ የጽሑፍ መልክት ተናግሮአል።

https://p.dw.com/p/4B6HE
Äthiopien Journalist Gobeze Sisay
ምስል privat

የፀጥታ ኃይላት አይኔን አስረዉ እቤቴ ደጃፍ ላይ ነዉ የለቀቁኝ


በመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች እሁድ ሚያዚያ 23 ቀን፣2014 ዓ.ም በቁጥጥር ሥር የነበረዉ ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ ለዘጠኝ ቀናት የነበረበት አድራሻ ጠፍቶ ቆይቶ ትናንት እራሱን ቤቱ ደጃፍ ላይ እንዳገኘ ገለፀ። በጤንነቱ ላይ ምንም ነገር እንዳልደረሰም ባስተላለፈዉ የጽሑፍ መልክት ተናግሮአል። ትናንት ሰኞ አመሻሹ ላይ ታፍኖ ከነበረበት በፀጥታ ኃይላት ዓይኑ ተሸፍኖ  ቤቱ በራፍ ላይ መጣሉ፤ ደንበኛዬ ከጠፋበት ቀን ጀምሮ ለምን እንደተያዘ በሕግ ለመጠየቅ የሚያስችል ምንም ነገር ባለማግኘቴ ሞያዊ ግዴታዬ እንዳልወጣ ሆኛለሁ ሲሉ ጠበቃዉ አማረዋል። ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ በፀጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር ከዋለ ቀናቶች  ቢያልፉም እስካሁን ፍርድ ቤት አለመቅረቡ እና ታስሮ የሚገኝበትን ቦታ ለማወቅ አለመቻሉ እንዳሳሰባቸው ጠበቃዉ ለዶቼ ቬለ ተናግረዉ ነበር። ጋዜጠኛ ጎበዜ ሲሳይ  የታጠቁ እና ሲቪል የለበሱ የመንግሥት ፀጥታ ኃይሎች ጋዜጠኛው ተከራይቶ ወደ ሚኖርበት ጊቢ በአጥር ዘለው ከገቡ በኋላ 'ለጥያቄ ትፈለጋለህ' ብለው ይዘውት ከሄዱ በኋላ ያለበት ቦታ ባለመታወቁ ቤተሰቡን እና በርካታ ዜጎችን አስጨንቆ መቆየቱ ብዙዎችን ሲያነጋገር የሰነበተ ጉዳይ ነበር። 
ሀና ደምሴ 
አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ