1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ጀርመን፤ የሄሰን የሰላም ሽልማት ለጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ

ሰኞ፣ መስከረም 12 2012

የዘንድሮው የጀርመኑ የአልበርት ኦስቫልድ ድርጅት የሄሰን የሰላም ሽልማት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሽልማት ተበረከተላቸው:: በሄሰን ግዛት ዋና መዲና ቪስባደን የፌደራል ግዛት ምክር ቤት ዛሬ በተከናወነው ልዩ የሽልማት አስጣጥ ሥነ ሥርዓት የኢትዮጵያ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሽልማት ተቀብለዋል::

https://p.dw.com/p/3Q7J5
Hessischer Friedenspreis wird an Abiy Ahmed Ali verliehen
ምስል DW/H. Melesse

በጠቅላይ ሚኒስትሩ ስም ሽልማቱን የተቀበሉት የኢትዮጵያ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል ናቸዉ

የዘንድሮው የጀርመኑ የአልበርት ኦስቫልድ ድርጅት የሄሰን የሰላም ሽልማት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ሽልማት ተበረከተላቸው:: ዛሬ ከቀትር በፊት በሄሰን ግዛት ዋና መዲና ቪስባደን በሚገኘው የፌደራል ግዛቱ ምክር ቤት በተከናወነው ልዩ የሽልማት አስጣጥ ሥነ ሥርዓት የኢትዮጵያ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚል የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሽልማት ተቀብለዋል:: በሽልማት አሰጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአልበርት ኦስቫልድ ድርጅት የሄሰን የሰላም ሽልማት  የቦርድ ስራ አመራር እና የሄሰን ፓርላማ ፕሬዝዳንት ቦሪስ ራየን ፤ "ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ለአፍሪቃ አህጉር ታላቅ ተስፋ ከተጣለባቸው መሪዎች አንዱ ናቸው" ሲሉ አመስግነዋቸዋል:: ለሃያ ዓመታት የዘለቀን እና ከ 100 ሺህ በላይ ሰዎች ያለቁበትን የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት በሰላም ለመፍታት ያደረጉት ጥረትና ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን መፍታታቸው እና በአገሪቱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚሳተፉበትን የፖለቲካ ምህዳር ማስፋታቸው ፤ በአገሪቱ የጀመሩት የፖለቲካና የምጣኔ ሃብት የተሃድሶ ለውጥ እንቅስቃሴም የሚደነቅ ነው ብለዋል:: ከዚህ ሌላ ኢትዮጵያ የሱዳን መንግሥትና ተቃዋሚዎችን በማሸማገል በሶማሊያ የሽብር ጥቃትን ለመከላከል በሚደረግ ዘመቻ እገዛ በማድረግ በደቡብ ሱዳንም እንዲሁ ሰላም ለማስፈን እና መንግስትንና ተቃዋሚዎችን ለማስማማት ያደረገችው ታላቅ ሚናም በአርአያነቱ ጎልቶ የሚጠቀስ ነው ሲሉ የሄሰን ፌደራል ግዛት ጠቅላይ ሚኒስትር ፎከር ቡፍየር የሄሰን በሥነ ሥርዓቱ ላይ አብራርተዋል::  ከ 16ቱ የጀርመን ፌደራል ግዛቶች አንዱ የሆነው የሄሰን ክፍለ ሃገር እንደ ጎርጎራውያኑ አቆጣጠር ከጥቅምት 16 ቀን፣ 1993 ዓ.ም ጀምሮ በቀድሞው የግዛቲቱ ጠቅላይ ሚኒስትር አልበርት ኦስቫልድ አማካኝነት የመሰረተው "የአልበርት ኦስቫልድ ድርጅት የሄሰን የሰላም ሽልማት " ላለፉት 25 ዓመታት በዓለም ሰላም እና በሰብአዊ አገልግሎት ተግባር ዙሪያ  የላቀ አስተዋጽዖ ላበረከቱ ግለሰቦች በየዓመቱ ሽልማት ሲሰጥ ቆይቷል:: ዘንድሮ ደግሞ ድርጅቱ የኢትዮጵያን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ ለሽልማት መርጦዋቸዋል:: ዛሬ ከቀትር በፊት በሄሰን ግዛት ዋና መዲና ቪስባደን በሚገኘው የፌደራል ግዛቱ ምክር ቤት በተከናወነው የሽልማት አስጣጥ ሥነ ሥርዓት ላይ የጀርመን መንግስት ባለስልጣናት የሄሰን ፓርላማ አባላት ልዩ ልዩ የጀርመን ፓርቲ ተጠሪዎች የዓለም አቀፍ ድርጅት ተወካዮች በጀርመን የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ወይዘሮ ሙሉ ሰለሞን እና ሎችም ዲፕሎማቶች እንዲሁም ታዋቂ ግለሰቦች የተገኙ ሲሆን የኢፌድሪ የሰላም ሚኒስትር ወይዘሮ ሙፈርያት ካሚልም የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሽልማት ተቀብለዋል:: የሄሰን የሰላም ሽልማት የስራ አመራር ቦርድ አባላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ የዘንድሮውን የሰላም ሽልማት አሸናፊ የሆኑባቸውን መሰረታዊ መስፈርቶች በሽልማት አሰጣጡ ሥነ ሥርዓት ላይ ለታደሙት የክብር እንግዶች በዝርዝር ገልጸዋል:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ስልጣን ከመጡበት ከመጋቢት 24ቀን፣ 2010 ዓ.ም ጀምሮ ከጎሳ ፖለቲካ ይልቅ ለአገራዊ ጉዳዮች ቀዳሚ ትኩረት መስጠታቸው እንዲሁም በአፍሪቃ ቀድም ሆነ በመላው አህጉሩ አስተማማኝ ሰላምና ልማትን ለማረጋገጥ ለውጭ ግንኙነት ፖሊሲያቸው ልዩ ትኩረት በመስጠት ከጎረቤት ኤርትራ ጋር ለ 20 ዓመታት የዘለቀውን ግጭት በሰላም ውል ለመቋጨት ያደረጉት ፈጣን እርምጃ በአርአያነት ጎልቶ የሚጠቀስ ታላቅ ተግባር ነው ተብሏል :: 105 ሚልዮን ያህል የልዩልዩ ብሔረሰቦች ሕዝብ በሚኖሩባት ኢትዮጵያ የፖለቲካ እና የምጣኔ ሃብት የተሃድሶ ለውጥ እንቅስቃሴ ማካሄዳቸው እና በያዝነው ዓመት ግንቦት ወር ነጻ እና ገለልተኛ ምርጫ ለማካሄድ ቃል በመግባት የዴሞክራሲያዊ ሥርዓቱን ይበልጥ ለማጠናከር ያላቸው ቁርጠኝነትም በአብነት ተጠቅሷል:: በመላው አገሪቱ ከ 4 ቢልዮን በላይ የዛፍ ችግኞችን በመትከል ተፈጥሮን ለመንከባከብ እና በረሃማነትን ለመከላከል የሚያደርጉትም አርዓያነት ያለው ተግባር በሽልማት ሥነ ሥርዓቱ ሌላው ላይ የተወሳ ጉዳይ ነበር:: የሄሰን የሰላም ሽልማት ድርጅት የሰላም እና ግጭት ምርምር ተቋም ኃላፊና የሽልማት ኮሚቴው የቦርድ አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ኒኮል ዳይትልሆፍ  "ዶክተር ዓብይ ሰላምን ለማስፈን ላላቸው ቁርጠኝነት አክብሮት መስጠት እንፈልጋለን " ሲሉ የዛሬ ወር ለሽልማት በተመረጡበት ወቅት ገልጸው ነበር:: ዛሬ ደግሞ በሽልማት አሰጣጥ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአልበርት ኦስቫልድ ድርጅት የሄሰን የሰላም ሽልማት የቦርድ ስራ አመራር እና የሄሰን ፓርላማ ፕሬዝዳንት ቦሪስ ራየን ፤ "ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ለአፍሪቃ አህጉር ታላቅ ተስፋ ከተጣለባቸው መሪዎች አንዱ ናቸው" ሲሉ አመስግነዋቸዋል:: "ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ለአፍሪቃ አህጉር ታላቅ ተስፋ ከተጣለባቸው መሪዎች አንዱ ናቸው፤  ለሃያ ዓመታት የዘለቀን እና ከ 100 ሺህ በላይ ሰዎች ያለቁበትን የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት በሰላም ለመፍታት ያደረጉት ጥረትና ፤ በሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞችን መፍታታቸው እና በአገሪቱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሚሳተፉበትን የፖለቲካ ምህዳር ማስፋታቸው ፤ በአገሪቱ የጀመሩት የፖለቲካና የምጣኔ ሃብት የተሃድሶ ለውጥ እንቅስቃሴም የሚደነቅ ነው "ብለዋል:: ከዚህ ሌላ ኢትዮጵያ የሱዳን መንግሥትና ተቃዋሚዎችን በማሸማገል በሶማሊያ የሽብር ጥቃትን ለመከላከል በሚደረግ ዘመቻ እገዛ በማድረግ በደቡብ ሱዳንም እንዲሁ ሰላም ለማስፈን እና መንግስትንና ተቃዋሚዎችን ለማስማማት ያደረገችው ታላቅ ሚናም በአርአያነቱ ጎልቶ የሚጠቀስ ነው ሲሉ የሄሰን ፌደራል ግዛት ጠቅላይ ሚኒስትር ፎከር ቡፍየር የሄሰን በሥነ ሥርዓቱ ላይ አብራርተዋል:: "ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ በአፍሪቃ ቀንድ ዘላቂ ሰላምን እና ልማትን ለማረጋገጥ በተለይም ለ 20 ዓመታት የዘለቀውን እና ከ 100 ሺህ ለሚልቁ ሰዎች ሞት ምክንያት የነበረውን የኢትዮ-ኤርትራ ግጭት በሰላም ስምምነት ለመፍታት ያደረጉት ቆራጥ እርምጃ በእጅጉ የሚመሰገን ነው:: " ብለዋል::

Hessischer Friedenspreis wird an Abiy Ahmed Ali verliehen
ምስል DW/H. Melesse
Hessischer Friedenspreis wird an Abiy Ahmed Ali verliehen
ምስል DW/H. Melesse
Hessischer Friedenspreis wird an Abiy Ahmed Ali verliehen
ምስል DW/H. Melesse

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ሽልማት የተረከቡት የሰላም ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል የጀርመኑ የሄሰን ፌደራል ግዛት በኢትዮጵያ ፈጣን የፖለቲካና የምጣኔ ሃብት ተሃድሶ እና ለውጥ እያስመዘገቡ ለሚገኙት ዶክተር አብይ ይህን ታላቅ ሽልማት በማበርከቱ የተሰማኝን ከፍተኛ ደስታ በጠቅላይ ሚኒስትሩ በአገሪቱ መንግስትና በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ስም ለመግለጽ እወዳለሁ ሲሉ ምስጋና አቅርበዋል::  ሽልማቱ ለኢትዮጵያ የሚንኖረውን ፋይዳ በተመለከተ እንዲገልጹልን ጠይቀናቸው ወይዘሮ ሙፈሪያት በሰጡት ምላሽ " ኢትዮጵያ በአገር ውስጥም ሆነ በክፍለ አህጉሩ የምታደርገውን የሰላም የልማትና የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እንዲሁም የለውጥ ሂደት ዓለም በሙሉ ተገንዝቦታል :: ከዚህ ሌላ የጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይን ጥረት እንዲሁም በኢትዮጵያውያን ተሳትፎ አማካኝነት ያገኘነውን ውጤትና ፍሬም የዓለም መሪዎች የተገነዘቡበት ሁነት ነው ሲሉ አስረድተዋል:: " ብለዋል::

የአልበርት ኦስቫልድ ድርጅት የሄሰን የሰላም ሽልማት ለአሸናፊዎች ከሚሰጠው የክብር ሽልማት ሌላ የ 25 ሺህ ዩሮ ተጨማሪ የማበረታቻ የገንዘብ ስጦታም ያበረክትላቸዋል:: ድርጅቱ ላለፉት 24 ዓመታት በዓለም ሰላም እና በሰብአዊ አገልግሎት ተግባር ዙሪያ የላቀ አስተዋጽዖ አድርገዋል ሲል ሽልማት ካበረከተላቸው ግለሰቦች መካከል የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን ምክትል ፕሬዝዳንት እና የህብረቱ የውጭ ጉዳዮች ሃላፊ ወይዘሮ ፌደሪካ ሞጎሮኒ በኢራን እና በዩናይትድስቴትስ መካከል በኑክሌር የጦር መሣሪያ መርሀግብር ስምምነት ዙሪያ የተፈጠረውን ውዝግብ በሰላም ለመፍታት ባደረጉት ጥረት፤   የቲቤታውያኑ የቡዳህ ዕምነት መንፈሳዊ መሪ ዳላይ ላማ በቻይና እና በቲቤት መካከል ለዘመናት የዘለቀው ውዝግብ በሰላም እንዲፈታ ላበረከቱት በጎ አስተዋጽዖ  ፤ የቀድሞዋ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ሳዳኮ ኦጋታ በዓለም ዙሪያ በሰብአዊ ቀውስ ውስጥ የሚገኙ ስደተኞን ለመርዳት ባደረጉት መልካም ተግባር፤ እንዲሁም አስረኛው የፊንላንድ ፕሬዝዳንት የኖቤል የሰላም ሽልማት ተሸላሚ እና የተባበሩት መንግስታት ዲፕሎማት የነበሩት ማርቲ ሃቲሳሪ ደም አፋሳሹ የኮሶቮ ጦርነት በሰላም ስምምነት እንዲቋጭ ላበረከቱት የላቀ ተግባር ሽልማት ከተበረከተላቸው ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው:: ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ባለፈው ዓመት ማገባደጃ ላይ በሄሰን የሰላም ሽልማት ያገኙትን 25 ሺህ ዩሮ ባለፈው ዓመት ማገባደጃ ለመልካም ወጣት ማዕከል ግንባታ ማበርከታቸው ይታወሳል ::

 

እንዳልካቸው ፈቃደ

ማንተጋፍቶት ስለሺ