ጀርመንን የለያየዉ ግንብ አሁንም አለ ይሆን?
ማክሰኞ፣ ኅዳር 2 2012ማስታወቂያ
ለ 40 ዓመታት በተለያዩ እና በተቃረኑ ስርዓቶች ዉስጥ ይኖሩ የነበሩ ጀርመናዉያን ከተዋሃዱ በኋላ ባለፉት ዓመታት በርካታ ነገሮችን በጋራ ለሃገሪቱ አካሂደዋል። ጀርመንን ለሁለት ርዕዮተ ዓለም የከፈለዉ ግንብ ከፈረሰ በኋላ የተለያዩ ቤተሰቦች ዳግም ተገናኝተዋል። ወጣቱ ትዉልድ በአሁኑ ወቅት ምዕራብና ምስራቅ ሳይል ፍቅር መስርቶ ትዳር መስርቶ ይኖራል። አንድነቱንም ተቀብሎ ምስራቅ ዉስጥ ተዘዋዉሮ ስራ ፈጥሮ ጓደኛና ኃብትን አፍሮቶ መኖር ጀምረዋል። እንድያም ሆኖ ሰሞኑን የወጣ አንድ የጥናት መዘርዝር እንደምያሳየዉ ከፋፋዩ ግንብ ፈረሰ እንጂ አሁንም በአንዳንድ ጀርመናዉያን ዉስጥ ልዩነት ይታያል። የጀርመኑ ርዕሰ ብሔር ፍራንክ ቫልተር ሽታይን ማየር ጀርመንን የከፋፈለዉ ግንብ የፈረሰበት 30ኛ ዓመት በሚታወስት እለት ባሰሙት ንግግር ህሊናችን ዉስጥ ያለዉን የልዩነት ግንብ ልናፈርስ ይገባል ሲሉ ተናግረዋል ። የእለቱ አዉሮጳና ጀርመን፤ ጀርመንን የለያየዉ ግንብ አሁንም አለይሆን? በሚል ርዕስ የምስራቅና የምዕራብ ጀርመንን የኑሮ ሁኔታ ያስቃኘናል፤ ለመሰናዶዉ የበርሊኑ የዶይቼ ቬለ «DW» ዘጋቢ ይልማ ኃይለሚካኤል ነዉ።
ይልማ ኃይለሚካኤል
አዜብ ታደሰ