የዓለም ዜና፤ መጋቢት 9 ቀን 216 ዓ.ም ሰኞ
አርስተ ዜናዎች፤
--የቀድሞው የሶማሌ ክልል ርዕሠ መስተዳድር በድንገት የተፈቱበትን ውሳኔ ኦነግ አጣጥሎ ነቀፈ። የታሰሩ አባሎቼ እስካሁን ክስ አልተመሰረተባቸዉም ሲል ከስዋል።
--ከሁለት ዓመት በፊት ከፈረንሳይ ግዛት በእንግሊዝ የባህር ወሽመጥ ላይ ከሰመጡ 27 ሰዎች መካከል የአንድ ኢትዮጵያዊ ቤተሰብ በፈረንሳይ መንግሥት ላይ ክስ መሠረተ። --የእስራኤል ኃይሎች ጋዛ ኧል ሺፋ ሆስፒታል ላይ ጥቃት ጀመሩ። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ስጋታቸዉን ገልፀዋል። --የ71 ዓመቱ የሩስያ ፕሬዚደንት በዓለማችን ፈላጭ ቆራጭ ከተባሉ ሃገራት መንግሥታት የእንኳን ደስ ያሎት መልዕክት ተቀበሉ። ሙሉዉን ዜና ይከታተሉ!