1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገ/እግዚአብሔር በወዳጆቻቸው አንደበት

ረቡዕ፣ መጋቢት 13 2015

ዶክተር ተወልደ ብርሀን ገብረእግዚአብሔር የብዝሀ ሕይወት ጉዳይ የሚገዳቸው፤ በዓለም አቀፍ መድረኮች በማደግ ላይ የሚገኙ 134 አገራትን ወክለው የተደራደሩ ሳይንቲስት ነበሩ። በዚህ ሣምንት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ዶክተር ተወልደ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና አስመራ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በተለያዩ ተቋማት በሙያቸው አገልግለዋል።

https://p.dw.com/p/4P511
Dr. Tewolde Berhan Gebre Egziabher
ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገ/እግዚአብሄር ምስል Privat

ስለ ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገ/እግዚአብሄር ማን ምን አለ?

የአካባቢ ጥበቃ ህይወት ሳይንቲስት የነበሩት በርካታ ዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ ሽልማቶችን  ባለቤት ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሔር  ለአገራችንም ሆነ ለዓለም አርሶ አደሮችን መብት ያስከበሩ የዘረ መል ማሻሻያ በተደረገባቸው ወይም የGMO ምግቦች ያላቸውን ተጽዕኖ አስመልክተው ውጤት ያለው ድርድር ያደረጉ ሳይንቲስት ነበሩ። በሥነ-ምህዳር ሳይንስ አያሌ ምሁራን ለአለም ያፈሩ እንዲሁም በርካታ መጽሃፍትን በመጻፍ፣ የአካባቢ ጥበቃ ስትራቴጂዎችን በመቅረጽ ለሀገር ያበረከቱ ሳይንቲስት ነበሩ።

የ83 ዓመት የእድሜ ባለፀጋ የነበሩትን ሳይንቲስት ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረ  እግዚአብሔር  ከአራት አስት አመታት በላይ እንደሚያውቋቸው ለዶቼ ቬሌ የተናገሩት ፕሮፌሰር እንዳሻው በቀለ ዶ/ር ተወልደ ብርሃን  ተቋምን ብቻ ሳይሆን አብረው ሰው የመሰረቱት ና ያፈሩ ትልቅ ሰው ናቸው ሲሉ በአገራችን ይሁን በአህጉር ደረጃ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ ናቸው  ብለዋል ካበረከቱት ስራዎች መሀከል ጥቂቶቹን አካፍለውናል።
«ባደጉት አገሮች መሀከል  ያለውን የብዙሃ ህይወት አጠቃቀም እና የመካፈል ወይንም አብሮ ቀጣይነት  እድገት ላይ ለመስራት ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረገ ነው።» አያይዘውም  «የአፍሪቃ አገሮች አስተባብሮ የተሟገተ ተሟግቶም ያሸነፈ በመጨረሻም አፍሪቃ የራስዋን እንብዛ ህይወት እንድትጠብቅ ያደረገ ሰው ነው» በአገራችንም ቢሆን ይላሉ ፕሮፌሰር እንዳሻው  «በኢትዮጵያ አካባቢ  ጥበቃ ላይ ብዙ ህጎች እንዲወጡ በአየር ለውጥ  ኢትዮጵያ ታወቂ ሆና አቅሟ እንዲጎለብት ያደረገ ትልቅ ሰው ነበር » ብለዋል። 

Dr. Tewolde Berhan Gebre Egziabher
ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገ/እግዚአብሄር ምስል Privat

የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያው ዶክተር ተወልደ ብርሃንን  ስራዎች  «የምድራችን ጀግና» በሚል በመጽሀፍ ያሳተመው ደራሲ ዘነበ ወላ ዶክተር ተወልደ ብርሃን በብዙሃን ህይወት ሀብት ላይ አፍሪካን ወክለው በአለም መድረክ ላይ ይቀርቡ ነበር ሲል ለዶቼ ቬሌ ተናግሯል የሚያውቁትም ይሁን የማያውቁት ሰው ሲስቅ ማየት ከምንም ነገር በላይ ያስደስታቸዋል ያለው ደራሲ ዘነበ የብዙዎች አባት ነበሩ ሲሉ ስለአገራቸው ነራቸውን ስሜት በዚ መልክ አጋርተውናል ።

«ከምንም ነገር በላይ የሚያሳስበው  የኢትዮጵያ አንድነት ነው»በጣም ብዙ ስራዎች ሰርተዋል ከነዚህ መሀከል ይላሉ ደራሲው «ኢትዮጵያ ከማዳበሪያ ገበያ ነጻ የሆነች ሃገር ለመፍጠር ያለፉትን 30 አመታት ጥረት አድርገዋል። ሌላው የማህበረሰብ መብት ና የአለም አርሶ አደሮች መብት ላይ ነው በብዙሀን ህይወት ላይ የባለቤትነት መብት ማውጣት ጀምረው ነበር ሌላው ሰው የፈጠረው ቁሶች ላይ ማውጣት ይቻላል በህያውያን ላይ ግን ማውጣት ገበሬውን እንደሚጎዳው ስለሚያውቅ ባደረገው ከባድ ክርክር ለውጤት አብቅተዋል »ብለዋል  ያስገኙትን ውጤት ሲናገሩ « በዓለም ላይ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን በላይ አርሶ አደሮችን የዘር መብት ባለቤትነታቸውን አረጋግጠዋል» ብለዋል ለበርካቶች አባት እና መጠለያ የነበሩት ዶክተር ተወልደ ብርሃንን የሕይዎት ጉዞ ዙሪያ ዳጎስ ያለ መጽሐፍአሳትመዋል ብለዋል።


ዶክተር ተወልደ ብርሃን  የዩናይትድ ኪንግደም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትን ጨምሮ በተለያዩ መድረኮች በመገኘት አካባቢ ጥበቃና ሥነ ህይወት የተመለከተ ንግግሮችን አድርገዋል በርካታ ስራዎችንም ለአለም አበርክተዋል ያሉት ፕሮፌሰር እንዳሻው በቀለ ዶክተር ተወልደ  ብርሃን ሳይንሱን በአገራችን ለማበልጸግ ትልቅ ስራ ሰርተዋል ይላሉ  «ሳይንሱን ለማበልጸግ ትልቅ ስራ ነው የሰራው። ትልቅ ሰው ነው። ብዙ የሰራ ሰው ነው በፍሎራው በኢኮሎጂው ፤ በቬጂቴሽን ለምሳሌ በደርግ ግዜ በጋንቤላ እና ዴዴሳ ኢኮሎጂው ቬጂቴሽን አሰርቷል ግን እሱ እንደሰራው አድርገን አይደለም የምንመለከተው ወይም ምናገናዝበው ሌላው በባዮ ቴክኖሎጂ ላይ በደንብ እውቀቱ ኖሮት ብዙ ስራዎችን እንዲሰራ ያደረገ ነው ለሃገሩ በርካታ ስራዎችን ያበረከቱ ሰው ነው»
ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ከአካባቢ ጥበቃና ብዝሃ ህይወት ጋር የሚያያዝ ከ30 በላይ ጥናቶችን አሳትመዋል። በተመሳሳይ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መጽሐፍትንም ጽፈዋል  እንዲሁም በርካታ ዓለም አቀፍና የአገር ውስጥ ሽልማቶችን አግኝተዋል።
እንደ አውሮፓውያኑ  አቆጣጠር 2000 ላይ ስዊዲን ስቶኮልም በአካባቢ ጥበቃ በነበራቸው አስተዋጽኦ አማራጭ (Alternative) የኖቤል ሽልማት የወሰዱ ሲሆን በ2006 ሲንጋፖር ላይ (champion of the earth) የሚል ሽልማትን ከመንግሥታቱ ድርጅት ተበርክቶላቸዋል።

Dr. Tewolde Berhan Gebre Egziabher
ዶክተር ተወልደ ብርሃን ገ/እግዚአብሄር ምስል Privat

ዶ/ር ተወልደ ብርሃን ገብረ እግዚአብሄር ከእናታቸው ከወ/ሮ ማእዛ ተወልደ መድኅን እና ከአባታቸው ከመምሬ ገብረ እግዚአብሄር ገብረ ዮሐንስ በሰሜን ኢትዮጵያ ትግራይ ክልል በአድዋ ከተማ አቅራቢያ በምትገኝ ይርባገረድ በተባለች አካባቢ የካቲት 12 ቀን፤ 1932 ዓ.ም ተወልደው በ83 አመታቸው መጋቢት 12 2013ዓት ቀን አረፉ ። የቀብር ስርአታቸው በአዲስ አበባ ከተማ የመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ቤተ ክርስቲያን ዛሬ ተፈጽሟል። ዶክተር ተወልደ የሦስት ሴት ልጆች አባት ነበሩ ።

ማኅሌት ፋሲል 

እሸቴ በቀለ