1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ፖለቲካሰሜን አሜሪካ

ዶናልድ ትራምፕ ምን ይጠብቃቸዉ ይሆን?

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 29 2013

የምርጫውን ውጤት መቀበል ተስኗቸው ሲያጣጥሉ የቆዩት እና ደጋፊዎቻቸውን በቁጣ ሲያነሳሱ ያሳለፉት ትራምፕ "ምንም እንኳ በምርጫው ውጤት ሙሉ በሙሉ ባልስማማም በጥር 12 ሥርዓቱን የጠበቀ ሽግግር ይደረጋል" ብለዋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፌስቡክ እና ኢንስታግራምን ከመሳሰሉ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ታግደዋል

https://p.dw.com/p/3neYf
US-Kapitol | Sturm der Trump-Fans
ምስል Win McNamee/Getty Images/AFP

ከአበበ ፈለቀ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

የአሜሪካ ኮንግረስ የጆ ባይንደንን የምርጫ ውጤት በይፋ አጽድቋል። ይኸ የሆነው ግን አክራሪ የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ደጋፊዎች የምክር ቤቱን ስብሰባ በኃይል ለማቋረጥ ከሞከሩ በኋላ ነው። በኹከቱ ፖሊስ አራት ሰዎች መገደላቸውን 50 ገደማ መታሰራቸውን አስታውቋል።

የምርጫውን ውጤት መቀበል ተስኗቸው ሲያጣጥሉ የቆዩት እና ደጋፊዎቻቸውን በቁጣ ሲያነሳሱ ያሳለፉት ትራምፕ ሥርዓቱን የጠበቀ የሥልጣን ሽግግር ይደረጋል ብለዋል። "ምንም እንኳ በምርጫው ውጤት ሙሉ በሙሉ ባልስማማም በጥር 12 ሥርዓቱን የጠበቀ ሽግግር ይደረጋል" ብለዋል። ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፌስቡክ እና ኢንስታግራምን ከመሳሰሉ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ታግደዋል። ትናንት በዋሽንግተን ዲሲ የተፈጠረው ቀውስ ራሷን የዴሞክራሲ ቁንጮ አድርጋ ለምታቀርበው አሜሪካ ምን ማለት ነው?

አበበ ፈለቀ

እሸቴ በቀለ

ነጋሽ መሐመድ