1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ የዘንድሮው የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት አሸናፊ

ሐሙስ፣ መስከረም 6 2014

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የጀርመን የአፍሪቃ ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ተገለጠ። ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ለሽልማት የበቁት በሕይወት ዘመናቸው ለአሰብአዊ መብቶች መከበር ላደረጉት አስተዋጽዖ መሆኑን የጀርመን የአፍሪቃ ሽልማት አዘጋጆች ባወጡት መግለጫ ዐሳውቀዋል።

https://p.dw.com/p/40MK4
Deutscher Afrika Preis 2021 - Daniel Bekele
ምስል Deutsche Afrika Stiftung

ከ30 በላይ እጩዎች መካከል ነው አሸናፊ የኾኑት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት አሸናፊ መሆናቸው ተገለጠ። ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ለሽልማት የበቁት በሕይወት ዘመናቸው ለአሰብአዊ መብቶች መከበር ላደረጉት አስተዋጽዖ መሆኑን የጀርመን የአፍሪቃ ሽልማት አዘጋጆች ባወጡት መግለጫ ዐሳውቀዋል። ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ከ30 በላይ እጩዎች መካከል አሸናፊ የኾኑት ከተለያዩ የፖለቲካ እና የመገናኛ አውታሮች በተውጣጡ 24 ገለልተኛ የዳኞች ቡድን ተመርጠው ነው።

ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ስለሰብአዊ መብቶች መሟገት የጀመሩት ገና በለጋ የወጣትነት እድሜያቸው በ23 ዓመት አዲስ አበባ ውስጥ በጥብቅና ሞያ ከተሰማሩበት ጊዜ አንስቶ እንደሆነ ሸላሚ ድርጅቱ ያሰራጨው መግለጫ ይጠቁማል። ከዚያን ጊዜ አንስቶ ለሰብአዊ መብቶች መከበር ላበረከቱት አስተዋጽዖ የጀርመን የአፍሪቃ ሽልማት አሸናፊ አድርጓቸዋል። ስቱዲዮ ከመግባቴ ቀደም ብሎ በግሎ ዶ/ር ዳንኤል በቀለን ካሉበት ስዊትዘርላንድ ጄኔቫ ደውዬ አነጋግሬያቸዋለሁ። ይህ ሽልማት ለእርስዎ ምን ትርጉ አለው? መጀመሪያ ያቀረብኩላቸው ጥያቄ ነበር።

ተሸላሚ ያደረገዎት «የጀርመን አፍሪቃ ተቋም» ፕሬዚደንት ዶ/ር ኡሺ አይድ የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት ማሸነፎን ባስተዋወቁበት ወቅት፦ «ገለልተኛ ዳኞች ድንቅ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች በመምረጡ ተደስቼያለሁ፤ ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በሕይወት ዘመናቸው ለሰብአዊ መብቶች ላደረጉት አስተዋጽዖ ሽልማቱ ይገባቸዋል» ብለዋል። ይህ ሽልማት ኢትዮጵያ ውስጥ የተከሰቱ የመብት ጥሰቶችን  ይፋ በማድረጉ ረገድ በዋና ኮሚሽነርነት ለሚመሩት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ምን አስተዋጽዖ ይኖረዋል? በተለይ ደግሞ አሁን ሀገሪቱ ውስጥ ከተከሰተው ግጭት አንጻር?

በሕይወት ዘመኖ ለሰብአዊ መብቶች መከበር ላደረጉት አስተዋጽዖ ተሸላሚ የኾኑት የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር በሆኑበት ወቅት ነው። ሽልማቱ እዚህ ጀርመን ውስጥ በደመቀ ሥነ ሥርዓት በከፍተኛ የጀርመን ፖለቲከኛ እጅ ነው የሚሰጠውር። ለአብነት ያህል ባለፈው ዓመት ተመሳሳዩ የጀርመን የአፍሪቃ ሽልማት ለ30 ዓመቷ ወጣት ሶማሊያዊት የመብት ተሟጋችና የበጎ አድራጎት ድርጅት መሪ ኢልዋድ ኤልማን የተሰጠው በጀርመን ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር እጅ ነበር። ሽልማቱን እዚህ ጀርመን መጥተው መቼ ነው የሚቀበሉት?

አንዳንድ ሰዎች ኮሚሽኑ ለመንግሥት ይወግናል ሲሉ ወቀሳ ያሰማሉ፤ ሌሎች ደግሞ በተቃራኒው መንግሥትን በነፍጥ የሚፋለሙ ወገኖችን ጥፋት ያድበሰብሳሉ ሲሉ ይደመጣል። ኮሚሽኖ ለሚቀርቡበት ለእነዚህ አይነት ወቀሳዎች አስተያየቶት ምንድን ነው? ከሽልማቱ ጋር አያይዘው ይግለጡልን።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

እሸቴ በቀለ