1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሕግ እና ፍትሕ

ድርጅቱ የኢትዮጵያ መንግስትን ሊከስ ነዉ

ረቡዕ፣ የካቲት 4 2012

የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ክሱን ለመመርመር ካቅማሙ ጉዳዩን ለአሐጉር አቀፍ ተቋማት አድርሶ መንግሥትን ሊሞግት ዝቷልም።ርዕሠ-መንበሩን ባንጁል-ጋምቢያ ላደረገዉ የአፍሪቃ የሠብአዊ መብቶች ኮሚሽን አቤት ማለቱንም አስታዉቋል

https://p.dw.com/p/3XfNm
Symbolbild Justiz Gericht Richterhammer
ምስል picture alliance/imageBROKER

የኢትዮጵያ መንግስት ሕግ ባለማስከበር ወንጀል ሊከሰስ ነዉ

የኢትዮጵያ የሕግ ማሕበረሰብ ለዕድገት የተባለዉ ድርጅት የኢትዮጵያ መንግሥትን የሰብአዊ መብት ጥሰትን በቸልተኝነት በማለፍ ወንጀል እንደሚከስ አስታወቀ።ከዚሕ ቀደም ብዙም የማይታወቀዉ የሕግ ተሟጋች ድርጅት እንደሚለዉ የኢትዮጵያ መንግስት በሕግ የተጣለበትን የዜጎችን ደሕንነት የማስከበር ኃላፊነቱን እየተወጣ አይደለም።የድርጅቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ንዋይ ግርማ እንዳሉት ድርጅታቸዉ በመንግሥት ላይ የሚመሰርተዉን የክስ ፋይል በቅርቡ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች ለመክፈት አቅዷል።የኢትዮጵያ ፍርድ ቤቶች ክሱን ለመመርመር ካቅማሙ ጉዳዩን ለአሐጉር አቀፍ ተቋማት አድርሶ መንግሥትን ሊሞግት ዝቷልም።ርዕሠ-መንበሩን ባንጁል-ጋምቢያ ላደረገዉ የአፍሪቃ የሠብአዊ መብቶች ኮሚሽን አቤት ማለቱንም አስታዉቋል።

ሰለሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

ሸዋዬ ለገሰ