1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዳግም ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ በሐረር 

ማክሰኞ፣ ሰኔ 25 2011

በሐረር ከተማ ዛሬ ጠዋት አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ በተለምዶ መብራት ኃይል የገበያ ማዕከል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተነሳ የእሳት ቃጠሎ በርካታ የንግድ ሱቆች መቃጠላቸውንና ለጊዜው ግምቱ በውል ያልታወቀ ንብረት መውደሙን የክልሉ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

https://p.dw.com/p/3LTkL
Screenshot Facebook Stadt Harare
ምስል Facebook/DW Amharic

በሐረር በንግድ ሱቆች ላይ የእሳት ቃጠሎ ሲደርስ የአሁኑ ለሦስተኛ ግዜ ነው። በገበያ ማዕከሉ በተለያየ ንግድ ተሰማርተው ሲሰሩ እንደነበር የገለፁ ነጋዴዎች ተከታዩን አስተያየት ሰተዋል ፡፡የሐረሪ ፖሊስ ኮምሽን የህዝብ ግንኙነት ዲቪዥን ሀላፊ ኮማንደር ጣሰው ቻለው ረፋድ ላይ በአደጋው ቦታ በሰጡት መግለጫ መከላከያ ሰራዊት አባላት ፣ ፌደራል ፖሊስና ህብረተሰቡ ባደረጉት ርብርብ እሳቱ መጥፋቱን ገልፀው ፤ የአደጋውን መንስዔም ሆነ በቃጠሎው የጠፋውን ውድመት በሚመለከት ምርመራ ተጣርቶ ለህዝብ እንደሚገለፅ ጠቁመዋል፡፡ በሐረር ከተማ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፣ አዳዲስ ጨርቆችን፣ የቤት መገልገያ ቁሳቁሶችና ሌሎች ሸቀጦች የሚሸጡበት የገበያ ማዕከል ቀድሞ ይገኝበት በነበረው እና ሸዋበር ተብሎ በሚጠራው ቦታ የደረሰበትን የመጀመርያ ግዜ ቃጠሎ ተከትሎ አሁን ወደሚገኝበት እና የክልሉ መብራት ኃይል ይዞታ ወደ ሆነው ቦታ መዛወሩን የሚገልፁ አንዳንድ ነጋዴዎች በቅርቡ መብራት ኃይል ከይዞታው ተነሱ በሚል ለጥፎት ነበር ባሉት ማስታወቂያ የአደጋ ስጋት አድሮብን ነበር የሚል አስተያየት አንስተዋል ፡፡የሐረሪ ክልል ኤሌክትሪክ አገልግሎት ስራ አስፈፃሚ ተወካይ አቶ ካሊድ ጠሀ የህዝቡን ጥያቄ በሚመለከት ከ«DW» ለቀረበላቸው ጥያቄ ተከታዩን ምላሽ ሰተዋል ፡፡በሌላ በኩል በገበያ ማዕከሉ ላይ የደረሰውን የእሳት ቃጠሎ ለመቆጣጠር ሰፊ ርብርብ ቢደረግም በተሌ የእሳት ማጥፊያ ተሽከርካሪው በአፋጣኝ የማጥፋት ስራ አልሰራም የሚል ቅሬታም ቀርቧል ፡፡ ቃጠሎው የደረሰበት ስፍራ በፀጥታ ኃይሉ ጥበቃ ስር መሆኑን ተመልክተናል።


መሳይ ተክሉ

አዜብ ታደሰ 

ኂሩት መለሠ