1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ደቡብ አፍሪቃ የሊቀመንበርነቱን ቦታ ትረከባለች

ቅዳሜ፣ ጥር 30 2012

እሁድና በሚቀጥለዉ ሰኞ በሚካሄደዉ 33 ኛዉ የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ደቡብ አፍሪቃ የኅብረቱን የ 2020 የሊቀመንበርነት ስልጣን ከግብፅ ትረከባለች። የአፍሪቃ ኅብረት የፕሬዚዳንትነት መንበር በየዓመቱ በዙር የሚያዝ ሲሆን፤ የግብጹ ፕሬዚዳንት ኧል-ሲሲ ስልጣኑን ለደቡብ አፍሪቃዉ አቻቸዉ ለሲሪል ራማፎዛ ያስረክባሉ።

https://p.dw.com/p/3XT0h
Südafrika Kapstadt World Economic Forum
ምስል picture-alliance/AP

ፕሬዚዳንት ራማፎዛ ስልጣኑን ከግብጹ አቻቸዉ ይረከባሉ

እሁድና በሚቀጥለዉ ሰኞ በሚካሄደዉ 33 ኛዉ የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ላይ ደቡብ አፍሪቃ የኅብረቱን የ 2020 የሊቀመንበርነት ስልጣን ከግብፅ ትረከባለች። የአፍሪቃ ኅብረት የፕሬዚዳንትነት መንበር በየዓመቱ በዙር የሚያዝ ሲሆን ባለፈዉ ዓመት የኅብረቱ ሊቀመንበር የነበረችዉ ግብጽ፤ ፕሬዚዳንት ኧል-ሲሲ ስልጣኑን ለደቡብ አፍሪቃዉ አቻቸዉ ለሲሪል ራማፎዛ ያስረክባሉ። ደቡብ አፍሪቃ የኅብረቱን ስልጣን በ2002 ዓ.ም ይዛ የነበረ ሲሆን ፤ በዝያን ወቅት የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ወደ አፍሪቃ ኅብረት የተዘዋወረበትም ጊዜ ይታወሳል። በዘንድሮዉ የኅብረቱ ሊቀመንበርነት ደቡብ አፍሪቃ ፤ ከግብጽ የተላለፉትን የኅብረቱን አጀንዳዎች በማስቀጠል ሰላምና መረጋጋትን ማስፈን በአፍሪቃ የጥይት ድምጽ እንዳይሰማ በማድረግ የአህጉሪቱን ሰላም ማረጋገጥ የሚለዉን አጀንዳ እንዲሁም ነፃ ንግድ ቀጠና የሚሉትን ቅድምያ ሰጥታ የምትሰራባቸዉ እንደሚሆኑ ተጠቅሶአል።

ገበያዉ ንጉሴ

አዜብ ታደሰ