1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ዩናይትድ ስቴትስ የኢትዮጵያው ጦርነት በፍጥነት መቋጫ እንዲያገኝ ትሻለች

ረቡዕ፣ ጥር 4 2014

ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት መቋጫ በሚያገኝበት መንገድ ላይ ትኩረት ሰጥታ በመሥራት ላይ መሆኗን አስታወቀች። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ኘራይስ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ወደ ፍፃሜ ለማምጣት አሜሪካ ጠንካራ ዲኘሎማሲ እየተከተለች ነው።

https://p.dw.com/p/45QvV
Das Weiße Haus in Washington
ምስል picture-alliance / dpa

ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ያለው ቀውስ ፈታኝ ሆኖ መቆየቱን አንድ ዲፕሎማት አስታወቁ

ዩናይትድስቴትስ በኢትዮጵያ የሚካሄደው ጦርነት መቋጫ በሚያገኝበት መንገድ ላይ ትኩረት ሰጥታ በመሥራት ላይ መሆኗን አስታወቀች። የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ኔድ ኘራይስ ትናንት ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ጦርነት ወደ ፍፃሜ ለማምጣት አሜሪካ ጠንካራ ዲኘሎማሲ እየተከተለች ነው። በሌላ በኩል በኢትዮጵያ ያለው ቀውስ ለዩናይትድስቴትስ ፈታኝ ሆኖ መቆየቱን አንድ የአሜሪካ አስተዳደር ከፍተኛ ባለሥልጣን መናገራቸው ተመልክቷል።

ታሪኩ ኃይሉ

ታምራት ዲንሳ

ማንተጋፍቶት ስለሺ