1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

ሰኞ፣ ሚያዝያ 18 2013

የፖለቲካ ፓርቲዎች ባቋቋሙት የጋራ ምክር ቤት  መሰረት በየሳምንቱ እየተገናኙ በክልላዊ እና የፖለቲካዊ ጉዳዩች ላይ ይመካከራሉ፡፡ከዓመት በፊት የጋራ ምክር ቤት ተቋቁሞ እንደነበር የተገናገሩት የምክር በቱ ጸሐፊ  በወቅቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጥያቄ እና ቅሬታን መፍታት ባለመቻሉ እንደ አዲስ ተቋቋሞ ከባለፈው አርብ አንስቶ ስራ መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3sbBl
Äthiopien | Kamil Hamid | Head of the Political Sector of Prosperity Party
ምስል Negassa Dessalegn/DW

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች አብሮ ለመስራትና መጪውን ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ለማድረግ ያስችላል ያሉትን  የጋራ  ምክር ቤት አቋቋሙ።የጋራ ምክር ቤቱ ሰብሳቢ የቤኒሻንል ጉሙዝ ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ካሚል ሀሚድ እንደተናገሩት የጋራ ምክር ቤቱን ያቋቋሙት ስድስት የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው። የምክር ቤቱ መቋቋም በፖለቲካ ፓርቲዎች የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በቀላሉ ለመፍታት ያስችላል ተብሏል፡፡ የቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ኃላፊ አቶ አመንቴ ግሺ የጋራ ምክር ቤቱ ጸሐፊ ናቸው። በክልሉ መተከል ዞን የመራቾች ምዝገባ አስካሁን አለመጀመሩም ተገልጸዋል።በክልሉ የመራጮች ምዝገባ ባልተጀመረባቸው አካባቢዎችም የአስፈጻሚዎች ስልጠና እየተከናወነ መሆኑና የቁሳስቁስ ስርጭት መጀመሩን ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማህበራዊ መገናኛ ዜዴ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

በፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል የሚፈጠሩ አለመግባባቶችን በቀላሉ ለመፍታት እና 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ሰላማዊ ለማድረግ በክልሉ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አቋቋመዋል። የጋራ ምክር በቱ ሰብሳቢ አቶ ካሚል ሀሚድ በፖለቲካ ፓርቲዎች የሚቀርቡ ቅሬታዎችንና አለመግባቦቶች በክልል ደረጃ ለመፍታት እና በክልሉ ሰላምን ለማስፍን የጋራ ምክር በቱ መቋቋም የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል ብለዋል፡፡ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ውስጥ ለምርጫ ከሚወዳደሩት ሰባት ፓርቲዎች መካከል የጋራ ምክር ቤቱን ያቋቋሙት ስድስቱ ናቸው፡፡ ከዚህ ቀደም በክልሉ በተለያዩ ጊዜያት በተፎካካሪ ፓርቲዎቸ የሚቀርቡ ቅሬታዎችን በቀላሉ የሚፈታ እንደሆነም አቶ ካሚል አብራርተዋል፡፡

የጋራ ምክር ቤቱ ጸሐፊ የሆኑት  የቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ ኃላፊ አቶ አመንቴ ግሺ በቤኒንሻል ጉሙዝ ክልል የሚንቀሳቀሱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባቋቋሙት የጋራ ምክር ቤት  መሰረት በየሳምንቱ እየተገናኙ በክልላዊ እና የፖለቲካዊ ጉዳዩች ላይ ይመካከራሉ፡፡ ከአንድ ዓመት በፊት የጋራ ምክር ቤት ተቋቋሞ እንደነበር የተገናገሩት የምክር በቱ ጸሐፊ  በወቅቱ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጥያቄ እና ቅሬታን መፍታት ባለመቻሉ እንደ አዲስ ተቋቋሙ ከባለፈው አርብ አንስቶ ስራ መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

በክልሉ መተከል ዞን እስካሁን  የመራጮች ምዝገባ እንዳልተጀመረም የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ገልጸዋል፡፡ የኢትዩጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባለፈው ዐርብ ይፋ ባደረገው መረጃ መሰረትም  እስካሁን የመራጮች ምዝገባ ባልተጀመረባቸው እና የጸጥታ ችግር ያለባቸው እንደ ምዕራብ ኦሮሚያ ሁሉም ወለጋ ዞኖች ባሉ አካባቢዎች የመራጮችን ምዝገባ ለማስጀመር እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ በቤኒንሻጉል ጉሙዝ ክልልም ከካማሺ ዞን ሴዳል ወረዳ ውጪ የመራጮችን ምዝገባ ለማካሄድ የቁሳቀስ ስርጭት እና የአስፈጻሚዎች ስልጠና እየተከናወነ ነው ብለዋል፡፡ የብልጽግና ፓርቲን ጨምሮ የቤኒሻንጉል ህዝቦች  ነጻነት ንቅናቄ፣የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ፣ የቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ እና ኢዜማ ዘንድሮ  በቤኒሻጉል ጉሙዝ   በ6ኛ ሀገራዊ ምርጫ ላይ የሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ናቸው።

ነጋሳ ደሳለኝ

ኂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ